የኮሪያ ኢንተርናሽናል ትብብር ኤጀንሲ (KOIKA) ለኢንስቲትዩቱ የሚያደርገውን ሁለተኛ ምዕራፍ ድጋፍ ለማስጀመር የሚያስችል ውይይት ተካሄደ።
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ብሩክ_ከድር የኮሪያ ኢንተርናሽናል ትብብር ኤጀንሲ (KOIKA) ሁለተኛ ምዕራፍ ትብብር ለማስቀጠል በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ በኢትዮጵያ የኮይካ ም/ዳይሬክተር በሆኑት ሺዮንግ ሊ ከተመራ የሀላፊዎች ቡድን ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ብሩክ_ከድር ፕሮጀክቱ በመጀመሪያ ምዕራፍ የሠራቸውን ስራዎች እና በቀጣይ የትብብር ፍላጎቶችን ለእንግዶቹ ገልጸዋል፡፡
የኮሪያ ኢንተርናሽናል ትብብር ኤጀንሲ (KOIKA) በኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በስድስት ትምህርት ክፍሎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ድጋፎችን ሲደርግ የቆየ ሲሆን ሁለተኛ ዙር ትብብር ለማስፋት በሚቻልበት ዙሪያ ውይይት የተደረገ ሲሆን በመንግስት እና የግል ተቋማት ትብብር (PPP) ማዕቀፍ ከኤልጂ ኮይካ (LG KOIKA) ጋር አብሮ ለመስራት፣ ተኪ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ለማምረት፣ የአገር ውስጥ እና የውጭ ገበያን መመለስ የሚችሉ ብቁ ዜጎን ለማፍራት፣ ኢንተርፕረነሪያል ቴክኒክና ሙያ ላይ በጋራ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር #ሐፍቶም_ገብረ_እግዚአብሔር (ረ/ፕሮፌሰር) ስለ ኢንስቲትዩቱ ተቋማዊ ነባራዊ ሁኔታ እና ትብብር ላይ ኢንስቲትዩቱ ያለውን ፍላጎት ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡