ኢንስቲትዩቱ ዲጂታል ልህቀትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ተገለጸ።
ኢንስቲትዩቱ ዲጂታል ልህቀትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ተገለጸ።
************ግንቦት 14/2016*************
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጥራት ያለው ስልጠናን ለማረጋገጥ ከሚሰራቸው ስራዎች ቁልፍ ከሚባሉት መካከል ዘመኑ የደረሰበትን የስልጠና ደረጃ የሚመጥኑ ጥራት ያላቸው የማሰልጠኛ መሳሪያዎችን ማዘጋጀት ተጠቃሽ ነው።
ላለፉት አራት ዓመታት ከተለያዩ አገርአቀፍ እና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት የአይሲቲ መሰረተ ልማቶችን ሲያሟላ፣ ለአሰልጣኞችም የአቅም ግንባታ ስልጠና ሲሰጥ የቆየው ኢንስቲትዩቱ በአሰልጣኞች እየተሰሩ ያሉ የኦንላይን ማስተማሪያዎችን ዝግጅት በየሳምንቱ በቋሚነት እየገመገመ ይገኛል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ብሩክ_ከድር በመጀመሪ ሳምንት የግምገማ መድረክe ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በኢንስቲትዩቱ ልህቀት ለማስመዝገብ ከሚሰሩ አንዱ ጥራት ያለው ስልጠና መስጠት አንዱ ነው፡፡ ዲጂታል ኮንተንቶችን በማዘጋጀት ገጽ ለገጽን ከኢንተርኔት ስልጠና ጋር አቀናጅቶ መስጠት ደግሞ ዲጂታል ልህቀት የሚያመጣ ተግባር ነው ብለዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አቅም ያለው እና ዘመናዊ ዳታ ሴንተር እንዲሁም በቅርቡ ዘመናዊ ዲጂታል ስቱዲዮ መገንባቱን፣ ለዲጂታል ስራዎች ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን የጠቀሱት ዶ/ር ብሩክ ከመሰረተልማት በተጨማሪ የሰውሀብት ልማቱ ላይ በስፋት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ በዚህም በወርክሾፖች በገጽ ለገጽ ከሚሰጥ ስልጠና ጎንለ ጎን በኢንተርኔት የስልጠና ስልት ስልጠናዎችን በመስጠት ጥራት ማረጋገጥ እንደሚገባ ለዚህም መልካም ጅምሮች እንዲጠናከሩ ጉድለቶች እንዲታረሙ መረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡
የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዋና ዳይሬክተር #ሐፍቶም_ገብረ_እግዚአብሔር (ረ/ፕሮፌሰር) በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ በMOPEDE ፕሮጀክት ድጋፍ አቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በማግኘት አሰልጣኞች ኮንተንቶችን እያዘጋጁ መሆኑን ጠቅሰው ተግባሩ ተቋማዊ ሆኖ ሳይቆራረጥ እንዲቀጥል ለማድረግ በትኩረት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡
ከ80 በላይ አሰልጣኞች ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ ኮንተንቶችን እያዘጋጁ እንደሚገኙ የጠቀሱት ም/ዋና ዳይሬክተሩ በየሳምንቱ ማክሰኞ በሚኖር መደበኛ መድረክ እየቀረቡ ውይይት እንደሚደረግባቸው፣ ልምድ እንደሚወሰድባቸው ተናግረዋል።




