ኢንስታትዩቱ በኢንተርኔት የማስተማሪያ ስልት (E-learning) የማስተማሪያ መሳሪያዎች ዝግጅት (Content Development) ያለበት ደረጃ ተገመገመ።

ኢንስታትዩቱ በኢንተርኔት የማስተማሪያ ስልት (E-learning) የማስተማሪያ መሳሪያዎች ዝግጅት (Content Development) ያለበት ደረጃ ተገመገመ።
የኢንስቲትዩቱ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዋና ዳይሬክተር #ሐፍቶም_ገ_እግዚአብሔር (ረ/ፕሮፌሰር) በኢንስታትዩቱ የገጽ ለገጽን እና በኢንተርኔት የማስተማሪያ ስልት (E-learning) በማቀናጀት የሚሰጡ ስልናዎች ያሉበትን ሁኔታ ገምግመዋል። አሰልጣኞችም የተሳኩ ጅምርቻቸውን፣ ተጥዳሮቶችን እና በቀጣይ ቢስተካከሉ ያሏቸውን አቅርበዋል።
ኢንስቲትዩቱ የተሰጠውን ጥራት ያለው ስልጠና የመስጠት ተልዕኮ ለማሳካት ዘመኑ በሚጠይቀው የስሕጠና ስርዓት መሠረት የገጽለገጽ ስልጠናው እና የኢንተርኔት የማስተማሪያ ስልትን (E-learning) በማቀናጀት እያሰለጠነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
የማስተማሪያ መሳሪያዎች ዝግጅት (Content Development) በMOPEDE ፕሮጀክት ሲደገፍ የቆየ ሲሆን በቀጣይነት በተቋሙ አቅም ለማስቀጠል ሁሉም በትኩረት መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።
በፕሮጀክቱ የተመረጡ አሠልጣኞች ከዚያ አኳያ መልካም ጅምሮች ቢኖሩም ከዚህ በላይ መስራት እንደሚገባ ተጠቅሷል። ኮንተንቶቹ ተዘጋጅተው መጫናቸው ብቻ ሳይሆን ሠልጣኞች በምን ደረጃ እየተጠቀሙባቸው እንደሆነም ተገምግሟል።
የአሰልጣኞችን ክህሎት ለማሳደግ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ፣ ከተለያዩ ተቋማት ጋር የልምድ ልውውጥ ስራ እንደሚሰራ ም/ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ይህንን ስራ የበለጠ አጠናክሮ ለመቀጠል ጠንካራ የክትትል ስርዓት የተዘረጋ ሲሆን ዘወትር ማክሰኞ በተቋም ደረጃ እንደሚገመገም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።