STEM Power Inauguration
ኢንስቲትዩቱ ሕጻናትን እና ወጣቶችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ስልጠና አብቅቶ ለቴክኖሎጂ ፈጠራ በማዘጋጀት የህብረተሰቡን ችግሮች መፍታት ያስችላል የተባለለት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ የስልጠና ማዕከል (STEM Center) አስመረቀ፡፡
********** ግንቦት 3/2016 ************
የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ የስልጠና ማዕከል (STEM Center) በኢትዮጵያ ከስልሳ በላይ ማዕከላት ያሉት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን በስልጠና እያበቃ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡ ማዕከሉ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ውስጥ የመጀመሪያ የሆነውን እና በአገር አቀፍ ደረጃ 61ኛ ማዕከሉን በኢንስቲትዩቱ ከፍቷል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ብሩክ_ከድር በማዕከሉ ይፋዊ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ‹‹በአገራችን ሳይንቲስቶችና ቴክኖሎጂስቶች እንዲፈጠሩ እና ችግር ፈቺ ምርምሮችን ማድረግ እንዲችሉ ይህ ማዕከል ትልቅ አገዛ ያበረክታል፡፡ ማዕከሉ ልጆችና ወጣቶች የቴክኖሎጂ ፍላጎታቸውን በማሳደግ ብቁ ዜጎች ሆነው እንዲድጉ ያስችላቸል ብለዋል።
እውቀት እና ችሎታ ኖሯቸው ችሎታቸውን የሚያወጡበት ማዕከል ያጡ ልጆችና ወጣቶች ብዙዎች ነበሩ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ አሁን ግን መሰል ማዕከላት ችግሩን እስከ ወዲኛው መቅረፍ እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ ማዕከሉ ስኬታማ ሆኖ ዜጎችን እንዲጠቅም አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደግም ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ሐብታሙ_ሙሉጌታ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ከሚሰራቸው በርካታ ተግባራት መካከል የህብረተሰቡን ችግሮች በቴክኖሎጂ መፍታት ተጠቃሽ እንደሆነ ገልፀው ይህንን ለማድረግ ወጣቶችንና ሕጻናትን በሳይንስና ቴክኖሎጂ በማሰልጠን በማብቃት ለቴክኖሎጂ ፈጠራ ለማነሳሳት ማዕከሉ መከፈቱ ትልቅ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
በዚህ ማዕከል የሚገቡ ህጻናትና ወጣቶች ፍላጎታቸውን መነሻ አድርገው ዕውቀታቸውን እንዲያዳብሩ፣ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ እንዲፈጥሩ፣ ሐሳባቸው ወደ ተግባር ተለውጦ ወደ ህብረተሰቡ ተደራሽ እስኪሆን ለመስራት ኢንስቲትዩቱ ሙሉ ዝግጁነት እንዳለውም ም/ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
የስተም ፓወር ሐገርአቀፍ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር #ስሜነው_ቀስቅስ ስቴም የስልጠና ማዕከላት በኢትዮጵያ እና በሌሎችም አገራት የሚሊዮኖችን ህይወት የቀየሩ ናቸው ያሉ ሲሆን የስልጠና አሰጣጡ ከሁሉም የትምህርት ደረጃዎች በበለጠ ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጋር ተያያዥነት ያለው በመሆኑ በዚህ ኢንስቲትዩት መከፈቱ ፋይዳው የላቀ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ማዕከላት ያሉት ቢሆንም በቴክኒክና ሙያ የመጀመሪያው እንደሆነ የገለፁት ዶ/ር ስሜነህ በኢትዮጵያ እና በሌሎች የአፍሪካ አገራት ከመቶ ሀያ በላይ ማዕከላት ያሉት ድርጅት ነው ብለዋል፡፡
ድርጅቱ እስከ ሁለት ዓመት ስልጠናዎችን እየሰጠ አንዳንድ ወጪዎችንም ድጋፍ እያደረገ የሚቆይ ሲሆን ከሁለት ዓመት በኋላ የተከፈቱባቸው ተቋማት በራሳቸው ይዘው የሚያስፋፏቸው እና የሚያዘልቋቸው እንደሆኑ ተናገረዋል፡፡
See Translation
