የሉባን የሥልጠና ማዕከልን ለማስፋ እንደሚሰራ ተገለፀ
በቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት የሚገኘውን የሉባን ስልጠና ማዕከል የማስፋትና የማጠናከር ስራ እንደሚቀጥሉ የቲያንጂን ቴክኖሎጂና ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢፌዲሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚንስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ለተመራው ልዑክ ስለመግለጻቸው
ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የምስራቅ አፍሪካ የEPIP (Engineering Practice Innovation Project) የሙከራ ማረጋገጫ ማዕከልን እንዲመሩ ኃላፊነት እንደተሰጣቸው ስለመገለጹ
የሉባን የሥልጠና ማዕከልን ለማስፋ እንደሚሰራ ተገለፀ
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የሚመራ የልዑካን ቡድን በቻይና የሥራ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል፡፡
የቻይና አፍሪካ የትብብር ማዕቀፍ አንዱ አካል የሆነው ስምምነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከዚህ ቀደም የተፈራረመ ሲሆን ስምምነቱን ወደ ስራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
በመድረኩ የቴክኒክና ሙያ ሥርዓተ-ትምህርት ቀረፃ፣ የተቋማት አቅም ግንባታ፣ የማሰልጠኛ መሳሪያዎች ድጋፍ እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ዲጂታላይዝድ ከማድረግ አኳያ እና ሌሎች በስምምነቱ የተመላከቱ ጉዳዮችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር ተመልክተዋል፡፡
ይህንን ተከትሎም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የEPIP (Engineering Practice Innovation Project) የቴክኒክና ሙያ ዘርፉን ከማገዝና ከማዘመን አኳያ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የሉባን ማዕከሉ እንዲስፋፋና እንዲጠናከር ጠይቀዋል፡፡
በዚህም በአዲስ አበባ በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት የሚገኘው የስልጠና ማዕከል ከተቋቋመ ጀምሮ እያደረገ የሚገኘው እንቅስቃሴ የሚበረታታ በመሆኑ ማዕከሉን የማስፋትና የማጠናከር እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ ማዕከላትንም የመክፈት ዕቅዱ እንዳላቸው የቲያንጂን ቴክኖሎጂና ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አመላክተዋል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የምስራቅ አፍሪካ የEPIP (Engineering Practice Innovation Project) የሙከራ ማረጋገጫ ማዕከልን እንዲመሩ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል፡፡
EPIP (Engineering Practice Innovation Project) የሙያ ስልጠናን ውጤታማ ለማድረግ በቲያንጂን ከተማ የተጀመረ እና በሉባን የሥልጠና ማዕከል ተግባራዊ የሚደረግ የማስተማሪያ ሞዴል ነው፡፡
የሉባን የሥልጠና ማዕክል በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢኒስቲትዩት ውስጥ ስራ የጀመረው እ.ኤ.አ 2011 የቻይና መንግስት ባደረገው የገንዘበ ድጋፍ ሲሆን ዓላማውም የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራንን በክህሎት ማብቃት ነው፡፡
የሉባን የሥልጠና ማዕከል የቻይና ቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች በሙያና ክህሎት የሚበቁበት ዋናው ቦታ በመሆኑ “the cradle of training vocational teachers in China” በመባል ይታወቃል፡፡