ኢንስቲትዩቱ የመምህራኖችን አቅም ለማሳደግ ቻይና የሚገኘው ቲያንጂን ዩንቨርስቲ በመላክ ሊያሰለጥን ነው፡፡ ቲያንጂን ዩንቨርስቲ በሜካትሮኒክስ የትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ ልምድ ሊያጋራ እንደሚችል አስታውቋል፡፡

Federal TVET Institute

October 28, 2019

የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከቲያንጂን ዩንቨርስቲ የተውጣጡ አባላት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም ሜካትሮኒክስ የትምህርት ዘርፍን ለማስፋትና ለማጠናከር በኢንስቲትዩት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን ሉባን ወርክሾፕ ተከላ ሊደረግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተሻለ በሬቻ እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነው ሉባን ወርክሾፕ ተከላ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ሟሟላቱ ጋር ተከትሎ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

በኢንስቲትዩቱ በኤሌክትሮኒክስ እና በሜካኒካል ትምህርት ዘርፎች ያሉትን መምህራኖች በሜካትሮኒክስ የትምህርት ዘርፍ ለመሰልጠን ወደ ቲያንጂን ዩንቨርስቲ ለመላክ የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

የቲያንጂን ዩንቨርስቲ የተውጣጡ አባላትም ሉባን ወርክሾፕ የሚሆን አስፈላጊውን ዘመናዊ ግብዓቶች፣ ማሽኖችን፣ በሟሟላት አብሮ የመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል
በቆይታቸው ቲያንጂን ዩንቨርስቲ ለኢንስቲትዩቱ ተማሪዎች የምትሰጠውን ነጻ የትምህርት ዕድል እና ቀደም ሲል የነበረውን የቴክኒክና ሙያ የክህሎት የትብብር ስልጠና አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም መክረዋል፡፡

የቲያንጂን ዩንቨርስቲ ተወካዮች ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ለመስራትና ያላቸውን ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያስችላቸውን የስምምነት ውል የተፈራረሙ ሲሆን በኢንስቲትዩቱ በኩል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ተሻለ በሬቻ ተፈራርመዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti