ስልጠናው ራሳችንን እንድንፈትሽ አስችሎናል፡፡ (ሠልጣኞች) የኢንስቲትዩቱ ተማሪዎች በሠላም ዙሪያ ውይይት እያካሔዱ ይገኛሉ፡፡

Federal TVET Institute

መስከረም 10/2012

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት ከተለያዩ አለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበር “Understanding Peace” በሚል ርዕስ ለተማሪዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ ስልጠናውን ከኢንስቲትዩቱ ጋር በትብብር ያዘጋጁት Universal Peace Federation፣ United for Human Rights እና Youth for Human Rights International የተባሉ ድርጅቶች እንደሆኑ የስልጠናው አስተባባሪ መምህር ወንድወሰን ተናግረዋል፡፡

በስልጠናው እየተሳተፉ ካሉት መካከል ከአይሲቲ ተማሪ መቅደስ ጫኔ ስልጠናው ራሴን ወደውስጤ እንዳይ አድርጎኛል ትላለች፡፡ ቤተሰቤ እንዴት እየተመራ እንደሆነ እንድፈትሽ አድርጎኛል በማለት ስልጠናው ከትምህርት ተቋም አልፎ ለማህበራዊ ህይወቷ ያለውን ፋይዳ ትናገራለች፡፡

‹‹ሠላም ከሌለህ አይደለም መማርና ማደግ ቤትህ መቀመጥ እንኳን አትችልም፡፡ በአንዳንድ የትምህርት ተቋማት ያየነው የሰላም መደፍረስ እንዳይደገም እንዲህ ያሉ ውይይቶች መካሔድ ይገባቸዋል፡፡›› ያለን ደግሞ ተማሪ እስራኤል ኩቱፋ ነው፡፡

ሰልጣኞቹ እንደሚሉት በትምህርት ተቋማት በመማሪያ ክፍሎችም ሆነ ከዚያ ውጭ እንዴት በሰላም መኖር እንደሚቻል፣ የሰዎችን ሀሳብ ስለመረዳት እና በሰላም ስለመሟገት በስፋት መስራት ይገባል፡፡
በስልጠኛው ላይ አነቃቂና አስተማሪ ንግግሮች፣ አስተማሪ ፊልሞች እና ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን ተመሳሳይ ስልጠናዎች በቀጣይም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ተብሏል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti