አካባያዊ ምቹ ሁኔታዎችን በመለየት እቅዶች ሊታቀዱ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡ ሳተላይት ተቋማት የ2012 በጀት ዓመት እቅዳቸውን ማቀድ ጀመሩ፡፡

Federal TVET Institute

02/13/11 ቢሾፍቱ

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት ከተቋቋመበት 2003 ዓ/ም ጀምሮ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞችን፣ አመራሮችንና የኢንዱስትሪ ቴክኒሽያኖችን እያፈራ አገራዊ ተልዕኮውን እየተወጣ ይገኛል፡፡ ከረጅም ጊዜ ስልጠናዎች በተጨማሪም አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት የእውቀትና ክህሎት ክፍተትን እየሞላም ይገኛል፡፡

የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞችና ኢንዳስትሪ ቴክኒሻኖች በአቅራቢያቸው የትምህርት እድል እንዲያገኙ እየተሰራ ባለው ስራ በ15 ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ሳተላይት ተቋማትን በመክፈት ተደራሽ እየሆነ የሚገኝ ክፍተኛ የትምህርት ተቋም ነው፡፡

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት ሳተላይት ተቋማት የ2012 በጀት ዓመት እቅድ ሁሉም የፋካሊቲ ኃላፊዎች እና የሳተላይት ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት በቢሾፍቱ እየታቀደ ይገኛል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የሳተላይት ተቋማት ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ዳኘው ውይይቱን በንግግር ሲከፍቱ የኢንስቲትዩቱን እቅድ ማሳካት የሚቻለው ሳተላይት ተቋማቱ በተሳካ ሁኔታ ሲፈጽሙ በመሆኑ ይህንኑ ግብ ሊያሳካ በሚችል መልኩ ሊያቅዱ ይገባል ብለዋል፡፡ 

ተቋማቱ በኢንስቲትዩቱ እቅድ ሳይታጠሩ ከራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዛመድ ሊያቅዱ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱን እቅድ በመነሻነት ያቀረቡት የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሲሳይ ክፍሌ ሲሆኑ "እያንዳንዱ አካባቢ የተለያዩ ምቹ ሁኔታዎችና ተፈጥሮ ሀብቶች ባለቤት ነው፡፤ ሐብቱን በጥልቀት በመለየት ህብረተሰቡን ሊጠቅም የሚችል እቅድ ማቀድ ይገባል"  ብለዋል፡" 

በተጨማሪም እቅዱ ሲዘጋጅ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመኑ የተያዙትን ግቦች ለማሳካት ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባ አቶ ሲሳይ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ከእቅድ ዝግጅት በኋላ የድጋፍና ክትትል አግባብ ምን መምሰል እንዳለበት በጥልቀት ውይይት ይደረግበታል ፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti