ውጤታማ ስራዎች ( project) ተግባራዊ እንዲሁኑ ለማድረግ የስርአተ ትምህርት ክለሳ ማድረግ የጎላ አስተዋጽኦ አለው ተባለ፡፡ የሲቪል ቴክኖሎጂ ፋከልቲ የክረምት መርሀ ግብር በስርአተ ትምህርት የይዘትና የትግበራን ችግር ተከትሎ የሚስተዋሉ ክፍቶችንና የመፍትሄ አቅጣጯዎች ላይ ትላንት መከረ፡፡

Federal TVET Institute

ነሀሴ 24ቀን 2011

በመድረኩ የሲቪል ቴክኖሎጂ ፋከልቲ ዲን አቶ ዳንኤል ጌታቸው እና በስሩ የሚገኙ ውድ ቴክኖሎጂ፣ ቢዩልዲንግ ቴክኖሎጂ፣ ሰርቬይግ ቴክኖሎጂ፣ አርክቴክቸራል ዲዛይን ቴክኖሎጂ፣ ዎተር ቴክኖሎጂ እና ሮድ ኮንስትራክሽን የትምህርት ክፍል ሀላፊዎች ተገኝተውበታል፡፡

በእለቱ ተማሪዎቹ በርካታ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ፣ ብቁና በቂ አሰልጣኝ እጥረት ፣የስርአተ ትምህርት የይዘትና የትግበራን ችግር ፣የክረምት ወቅት ፕርጀክት ለመስራት አመቺ አለመሆን፣ የተመራቂ ተማሪዎች የቆይታ ጊዜ ፣ የተማሪዎች ውጤት ፣ የመመረቂያ ስራዎች ርእስ ማስገቢያ ቀን መዘግየት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ 

በመድረኩ የሲቪል ቴክኖሎጂ ፋከልቲ ዲን አቶ ዳንኤል ጌታቸው በበኩላቸው ስርአተ ትምህርትን በተመለከተ በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሰረት ክለሳ የተጀመረ በመሆኑ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችሉ መፍትሄዎች እንደሚያካቱ ተናግረዋል፡፡

በተያያዘም በየአመቱ የሚማሩትን የትምህርት አይነቶችን ለተማሪዎች በየጊዜው ከማሳወቅ ጋር የነበረውን የመረጃ ክፍተት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተመለከተ በቀጣይ ተማሪዎቹ በኢንስቲትዩቱ ባሉት ማህበራዊ ድረገጾች በመጠቀም ማሳወቅ እና ለሁሉም ተደራሽ የሚሆንበት መንገድ እንደሚፈጠር ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች ዘመኑ ደረሰበትን እውቀትና ክህሎት እንዲይዙ ከመምህር ጠባቂነት አመለካከት ወጥተው እየተማሩ ባሉበት የሙያ ዘርፍ ላይ ትኩረት ሰጥተው ራሳቸውን ማሳደግና ማብቃት እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
የዲፓርተትመንት ሀላፊ መምህራኖችም በበኩላቸው በትምህርት ጥራት እና በመማር ማስተማር ሂደት ላይ የተነሱ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ የሰጡ ሲሆን ዘርፉን በቀጣይ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የበኩላቸውን ለማበርከት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮ የትምህርት ዘመን በሲቪል ቴክኖሎጂ ስር የሚገኙ ስድስት የትምህርት ክፍሎች በአጠቃላይ 294 ተማሪዎችን በመደበኛዉ አስመርቀዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti