የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኮሌጅ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር የኢንደስትሪዎችን ምርታማነት ለማረጋገጥ ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገለጸ፡፡

Federal TVET Institute

ነሀሴ 23 ቀን 2011ዓ.ም

የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክ ሳተላይት ኮሌጅ ዋና አስተባባሪ አቶ ይልማ ጥላሁን እንደገለጹት በ2011 የትምህርት ዘመን በማኑፋክቸሪግ የትምህርት ክፍል በተመራቂዎችን የተሰሩት ማሽኖች ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራዞች ችግር ፈቺ በመሆናቸዉ ጥሩ ጅምር ነው፡፡

ኮሌጁ የኢንደስትሪዎች ምርታማነት እንዲረጋገጥ ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ወቅት ውጤት ተኮር ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል አስፈላጊውን የሰው ሀይል እና የጥሬ እቃ አቅርቦት ግብዓቶች እንዲመዋሉ የሚመለከታቸው አካላት ርብርብ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል-አቶ ይልማ፡፡

ኮሌጁ ተማሪዎች በእውቀት ፣በክህሎትና በአመለካከት የታነጹ ስራ ፈጣሪ፣ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎች እንዲሆኑ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

በማኑፋክቸሪግ የትምህርት ክፍል ለመጀመሪያ ጊዜ በዲግሪ መርሀ ግብር አስተምሮ ያስመረቃቸው ተማሪዎች ከምርቃታቸው ቀን ቀደም ብሎ የተለያዩ ችግር ፈቺ ናቸው ያልዋቸውን የቴክኖሎጂ ስራዎቻቸውን ለህዝብ እይታ አቅርበዋል፡፡ 

ለእይታ ካቀረቡዋቸው ስራዎች መካከል የከባባድ እቃ ማንሻ እና ማጓጓዧ፣ጡብ ማምረቻ፣ ለመስኖ ስራ የሚውል ውሀ ማውጯ እና ወንፊት በመቀያየር እህል እና አሸዋ ማበጠሪያ ማሽኖች ይገኙበታል ፡፡

እነዚህም ለእይታ የቀረቡት ማሽኖች የተማሪዎቹ የመመረቂያ ስራዎች ሲሆኑ ተጀምዉ እስከሚጠናቀቁ ድረስ ባለው ሂደት የመምህራኖቻቸው እገዛ እና አስተዋጽኦ ላቅ ያለ እንደነበር ተናግረዋል ፡፡

ሳተላይት ተቀሙ ለመጀመሪያ ጊዜ በዘንድሮ በጀት አመት ማኑፋክቸሪንግ ትምህርት ክፍል 26 ከጋርመንት የትምህርት ክፍል 11 በድምሩ 37 ተማሪዎችን አስመርቀዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti