የክረምት መርሀ ግብር የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የትምህርት አሰጣጡ በተያዘው መርሀ ግብር መሰረት ሊያልቅ አይችልም ሲሉ ስጋታቸውን ገለጹ፡፡

Federal TVET Institute

ነሀሴ 22 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢንስቲትዩቱ አካዳሚክ ምክትል ዋና ዳሬክተር አቶ ሀብቶም ገ/እግዝያብሄር ከክረምት ተማሪ ተወካዮች ጋር በተወያዩበት ወቅት በመርሀ ግብሩ መሰረት ስልጠናዉን ለማጠናቀቅ ያስቸጋራል ሲሉ ተማሪዎቹ ቅሬታቸዉን ገልጸዋል፡፡ 

ከመምህራን የስራ ጫና የተነሳ ያልተሸፈኑ ምእራፎችና ቀሪ የመመረቂያ ስራዎቻቸውን ለማከናወን በቂ ጊዜ እንዲሚያስፈልጋቸውም ተናግረዋል ፡፡

የተማሪዎቸቹን ጥዯቄ ተከትሎ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብቶም በሰጡት ምላሽ ከቀጣይ መንፈቅ ዓመት በሁዋላ ተማሪዎች መጥተው እንዲማሩ ለማድረግ ኢንስቲትዩቱ አማራጨችና ተሞክሮዎችን እያየ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የክረምት መርሀ ግብር ትምህርት በአምስት ክረምት እና በ4 ብሎክ ኮርስ እንዲሰጥ የታቀደ ቢሆንም ያለባቸዉን የዶርም፣ የመምህራን ውጥረትና ፣በጀት ችግር በማገናዘብ በቀጣይ ምላሽ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡ 

በቀጣይ ዓመት በክረምት መርሀ ግብር ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ተማሪዎችን ኢንስቲትዩቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስመርቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti