በቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች የሚታየውን የሙያ እና የክህሎት ክፍተት ለመቅረፍ የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና ሊጀመር ነው፡፡

Federal TVET Institute

ነሀሴ 21 ቀን 2011

GIZ STAP 2 GOPA የተሰኘ የጀርመን ድርጅት ኢንስቲትዩቱን ጨምሮ ከሳተላይትና ከክልል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተውጣጡ በሙያ እና በስራ አፈጻጸም ብቁ የሆኑ 150 አሰልጣኝ መምህራንን ለማሰልጠን እቅድ ማዘጋጀቱን ገልጹዋል፡፡

ስልጠናው ከዚህ ቀደም መምህራኖች ላይ የሚታየውን ከእውቀትና ከክህሎት አቅም ማነስ ጋር ተያይዞ በትብብር ስልጠና ሂደት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ውስጥ ያለውን ችግሮች የሚቀርፍ ነው ተብላል፡፡
GIZ stap 2 GOPA ሲንየር አድቫዘር አየለ አበበ(ዶ/ር) እንደገለጹት ከተመረጡ የሙያ መስኮች ማለትም ሜታል ማኑፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ እና ጨርቃጨርቅ ቆዳና ቆዳ ውጤቶች የትምህርት አይነቶች የተውጣጡ 150 ብቁ መመህራን ናቸው፡፡

የስልጠናው ዋና አላማ በማስተማር ላይ ያሉ መምህራኖችና ወደ ስራ የሚሰማሩ ባለሙያዎች በስራው አለም የሚፈልገውን ሙያና ክህሎት ይዘው በአገሪቱ ኢንዱስትሪና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ ማበርከት የሚያስችል ባለሙያ መቅረቡን ማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡

የስልጠና መረሀ ግብር በተመለከተ የትብብር ስልጠና ምንነት፣ ችግሮችን መለየት፣ የማቀድ ፣የመተግበርና ፣የመመዘን በተሰኙ የማሰተማሪ ሰነዶች(ሞጁል) ላይ መምህራኖቹ በቡድን ተወያይተው አዳዲስ ሀሳቦች እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡

በአጠቃላይ ለ20 ቀናት የሚቆየው ይሀው ስልጠና መምህራኖች በመሰረታዊ የማስተማር ክህሎት፣ የቴክኖሎጂ ክህሎትና የኢንደስትሪ ትስስርና ቁርኝት ላይ በቂ ግንዛቤና እውቀት እንደሚያገኙበት ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ 
ስልጠናው የሚሰጥባቸው ከተሞች የተለዩ ሲሆን በአዲስ አበባ፣ ሀዋሳ፣ ባህር ዳር፤ አዳማ፣ መቀሌ እና በጅማ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

ሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ ተከታትለው ሲጨርሱ በፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት አማካኝነት የምስክር ወረቀት የሚበረከትላቸው መሆኑ ታውቀል፡፡ 

በውይይቱ የተነሱ የማስተካከያ እና ሌሎች የተጨመሩ አዳዲስ ሀሳቦች ተካተዉ በቅርቡ ወደ ተግባር እንዲሚገባ ታውቋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti