የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠናዎች ከ12ኛ ክፍል በኋላ እንደሚጀምር ተገለጸ

Federal TVET Institute

August 21, 2019

የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቲቪቲ ሁሉም ስልጠናዎች ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላ እንደሚጀምሩ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ትምህርት መርሃ ግብር ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 8 ወይም እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ደረጃ ድረስ መማር እንደሚችሉ ነው የተገለጸው፡፡

በሌላ በኩል መምህራን ባላቸው የትምህርት ደረጃ ላይ መሰረት በማድረግ የመምህራን ድልድል መሰራቱም ተገልጿል፡፡

በዚህም የአንደኛ ደረጃ ከመምህራን የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው፣ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲ መምህራን ሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያላቸው እንደሚመደቡ ተገልጿል፡፡
(EBC)

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti