የምህንስና ልህቀት ማእከል የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት አካል ሆኖ በመስራት ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

Federal TVET Institute

ነሀሴ 3 ቀን 2011

ማእከሉ ከዚህ ቀደም ከፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ጋር ይሰራ የነበረ ሲሆን ከግንቦት ወር ጀምሮ የኢንስቲትዩቱ አካል እንደሆነ ተገልጸል፡፡ 

የብየዳ ቴክኖሎጂ ማእከል ሀላፊ አቶ ማትዮስ አሸናፊ እንደገለጹት ማእከሉ የቴክኖሎጂን ቅጂ እና ለክልል ሰልጣኞች የብየዳ ስልጠና መስጠት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል፡፡

እንደ አቶ ማቲዮስ ገለጻ ማእከሉ ከኤጀንሲ ይልቅ የኢንስቲትዩቱ አካል ሆኖ ቢሰራ ይበልጥ ውጤታማ እንደሚሆን ታሳቢ በማድረግ በሳይንስና በከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል ጸድቋል ፡፡ 

በማእከሉ ውስጥ ቴክኖሎጂ የመቅዳትና የማምረት ስራዎችን በማከናወን የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማትና በዘርፉ የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲበቁ እየተደረገ ነው በዚህም ተወዳዳሪነታቸው እያየለ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ከኢንስቲትዩቱ ተልእኮ ጋር ተያያዥነት ያለው በመሆኑ ተቀላቅሎ መስራት እንዳስቻላቸው ገልጸዋል፡፡ 

በማእከሉ ውስጥ ዌልዲንግ እና ማኑፋክቸሪግ ቤተሙከራዎች ያሉ ሲሆን ብየዳ ክፍል ላይ 5 ዌልዲንግ ኢንጅነሮች አጠቃላይ 69 ሰራተኞች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

በማማርና እድገትን አስመልክቶ በባህርዳር ዩንቨርስቲ ለ14 አሰልጣኞች በድህረምረቃ የትምህርት መርሀግብር ነጻ የትምህርት እንድል ተጠቃሚ እንደሆኑ ገልጸዋል አቶ ማቲዮስ፡፡

በቀጣይ giz ተባለ የጀርመን ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን በርካታ ባለሙያዎችን ከሀገር ውጪ በመላክ እንዲሰለጥኑ ማድረግ እና የብየዳ ስራዎችን በተመለከተ ባለሙያዎችና የብየዳ ቤተሙከራዎች የብቃት ማረጋገጫ እውቅና እንዲሰጥ ማስቻል ትኩረት አድርገን የምንሰራቸው ተግባራት ናቸው ሲሉ አቶ ማቲዮስ ገልጸዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti