ኮሌጁ ከ298 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

Federal TVET Institute

July 12, 2020

የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል፡፡

ኮሌጁ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መረጃ እንዳመለከተው ከ298 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ የወረርሽኑን ስርጭትን ለመቀነስ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ነው፡፡

በዚህም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ ከንክኪ የፀዳ የእጅ መታጠቢያ፣ ለለይቶ ማቆያ አገልግሎት የሚሆኑ አልጋዎችና የተለያዩ አልባሳትን በማዘጋጀት ለተቋሙ ሰራተኞች፣ ለአካባቢው ማህበረሰብና ለከተማ ኮቪድ መከላከል ግብረ-ሃይል ማሰራጨት ችሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ለኮምቦልቻ ከተማ እና ለቃሉ ወረዳ አስተዳደር ኮቪድ መከላከል ግብረ-ሃይል 130 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

የሰራተኞቹንና የአሰልጣኞቹን ደህንነት ለመጠበቅም የተለያዩ የጽዳት መጠበቂያ ግብዓቶች ማቅረቡን ኮሌጁ ያደረሰን መረጃ ያመክታል፡፡
(FTA)

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti