የኢንስቲትዩቱ የስራ ኃላፊዎች በወቅታዊ አካዳሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ በzoom ውይይት አካሔዱ፡፡

Federal TVET Institute

ግንቦት 5/2012

ፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩ የስራ ኃላፊዎች በየሁለት ሳምንቱ በቋነሚት በzoom አማካይነት ውይይት ያካሂዳሉ፡፡ በትላንትናው እለትም የአካዳሚክ ዳይሬክቶሬቶች፣ ፋካሊቲ ዲኖች እና ትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ውይይት አካሂደዋል፡፡

የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሀብቶም ገ/እግዚአብሔር እንደገለፁት ሦስት አጀዳዎች ላይ ውይይት የተካሔደ መሆኑን እነዚህም የተመራቂ ተማሪዎች የምርምር ስራዎች (thesis) እና ፕሮጀክቶች (project) ያለበት ሁኔታ፣ 1ኛ ዓመት የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ኮርስ ያለበት ሁኔታ እንዲሁም የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የonline ትምህርት ያለበት ሁኔታ እና ለውጦች ተገምግመዋል፡፡

አቶ ሀብቶም ሁሉም ተግባራት እድገት ማሳየታቸውን ጠቅሰው ተመራቂ ተማሪዎች ከአማካሪዎቻቸው ጋር ግንኙነት መጀመራቸውንና በዚህ ዓመት የሚጨርሱና የማይጨርሱትን የመለየት ስራ ተጠናቅቋል፡፡ መጨረስ ለሚችሉትም አስፈላጊውን ፋይናንሰ ለመመደብ መስማማታቸው ታውቋል፡፡

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በፈጠረው ችግር ምክንያት በዘርፉ የተከሰተውን ለውጥ ተከትሎ የትምህርት ካላንደር ለመከለስ ኮሚቴ ተዋቅሯል፤ የተገኘው ግብአት ለሴኔት ቀርቦ ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል ብለዋል አቶ ሀብቶም፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti