የኢንስቲዩቱ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶረት አስተባባሪ ሆኖ ሚያዝያ 23 2012 ዓ.ም ለየካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ማሃበረሰብ ኮቪድ-19ን መከላከል የሚረዳ ድጋፍ ተደርጉዋል፡፡

Federal TVET Institute

May 02, 2020

የክ/ከተማዉ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋዉ ለገሰና የወረዳ 9 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እንግዳወርቅ ሀይሉ በኢንስቲትዩቱ ተገኝተዉ ድጋፉን ተቀብለዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተሻለ በሬቻ፣የቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ እንየዉ ጌትነት፣ የአካዳሚክ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀፍቶም ገ/እግዚያብሄር፣ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶረት ዳይሬክተር ዶር. ገነነ አበበ እና ለሎች የኢንስቲትዩቱ ማህበረሰብ ተገኝተዋል፡፡

ድጋፉ የተደረገዉ 40 ሺ ብር ወጪ ከመምህራንና ሰራተኞች 100 ሺ ብር ወጪ ከኢንስቲትዩቱ ተደርጎ ምግብና ምግብነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ግዥ ተደርጎ ነዉ፡፡ በዚህም 50 ኩንታል ዱቄት፣ 100 ሊትር ዜይት፣ 300 የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እና ያለእጅ ንክኪ የሚሰራ እጅ ማስታጠብያ በሀላፊዎች በኩል ለማህበረሰቡ እንዲደርስ ተደርጉዋል፡፡

በቀጣይም ድጋፎችን ለማድረግ ኢንስቲትዩቱ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑ ታዉቆአል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti