አርባምንጭ ሳተላይት ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ የኮሮና ቫይረስን (covid-19) ለመከላከል የሚያግዙ ቁሳቁሶችን ለዞኑ አስተባባሪ ኮሚቴ አስረከበ፡፡

Federal TVET Institute

April 28, 2020

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት በዋናው ግቢና በሳተላይት ተቋሞቹ የኮሮና ቫይረስን (covid-19) ለመከላከል የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

አርባምንጭ ሳተላይት ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅም ከሰሞኑ የኮሮና ቫይረስን (covid-19) ለመከላልና ለመቆጣጠር ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየሰራ ሲሆን በተጨማሪም ለዞኑ ኮቪድ መቆጣጠሪያ ኮማንድ ፖስት ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን አስረክቧል፡፡

ኮሌጁ የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች መምህራንን በማሳተፍ የሰራቸውን ሁለት ሺህ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች እንዲሁም ከንክኪ የፀዳ እና በአንድ ጊዜ ሁለት ሰዎችን ማስታጠብ የሚስችሉ ሃያ ስድስት መታጠቢያዎች ያስረከበ ሲሆን በቀጣይም ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
=============================================================================================================

Arba Minch polytechnic satellite college submitted covid-19 preventive materials to the zonal committee.
-------------------------------------
Federal TVET Institute is contributing various activities from its main campus and satellite campuses to protect covid-19.
The one, Arba minch satellite polytechnic college, has been working awareness creation on preventing Covid-19, while also submit a variety of materials to the Zonal Co-Control Command.

The college, in this week, submitted two thousand masks, and twenty-six pedal hand-wash materials. And the college further stated to continue to strengthen its activities.

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti