ኢንስቲትዪቱ ማቆያዎችን ለለይቶ ማቆያ አስተባባሪ ኮሚቴ አስረከበ።

Federal TVET Institute

ሚያዚያ 10/2012

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዪት ኮሮናን (Covid-19) የመከላከል አገራዊ ስራን ለማገዝ ያዘጋጃቸውን ማቆያዎች ዛሬ ለለይቶ ማቆያ አስተባባሪ ኮሚቴ አስረክቧል።

ኢንስቲትዪቱ በዋናው ግቢና በሳተላይት ተቋሞቹ ኮሮናን (Covid-19) ለመከላከል የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን እያመረተ የኢንስቱትዩቱንና የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ሲያደርግ ቆይቷል ። በዚህም የፊት መሸፈኛ ጭምብሎችንና ያለ እጅ ንክኪ እጅ መታጠብ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ለአገልግሎት አብቅቷል።

ዛሬ ሚያዚያ 10/2012 ዓ.ም ደግሞ ዝግጁ አድርጎ ያቆያቸውን ማቆያዎች የሳይንስና ከፍተኛ ተምህርት ሚንስትር ፕ/ር ሂሩት ወ/ማርያምን ጨምሮ የኢንስቲትዪቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ለለይቶ ማቆያ አስተባባሪ ኮሚቴ አስረክቧል።

(ፎቶ:- ጠቅላይ አቃቤ-ህግ አዳነች አቤቤ የፌስቡክ ገጽ)


Watch the Video: 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti