ኢንስቲትዩቱ በፌደራል የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ዙሪያ ለሰራተኞች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

Federal TVET Institute

March 9, 2020

በስልጠናው ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰይፉ ታደሰ ስልጠናው ሰራተኛው ግዴታውን በአግባቡ አውቆ መብቱን የሚጠይቅ እና በስራ ውጤታማ እንድሆኑ እና መልካም የስራ ከባቢ ለመፈጠር ታስቦ ነው፡፡

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በሀገራችን ዘመናዊ ሲቪል ሠርቪስ በ1907 ዓ.ም እንደ ተመሠረተ እና ደንብ ቁጥር 1/55 ለ 40 አመት እንዳገለገለ ገለጻ ያደርጋል፡፡
የቆየው አዋጅ በፌደራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ 262/94 እንደተከለሠ እና በአዋጅ 515/99 እንተሻሻለ እንድሁም በአፈፃፀም ላይ የታዩትን ችግሮች ለመቅረፍ በአድሱ የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ 1064/2010 እንደተተካ የኮሚሽኑ የሰውሀብት ህጎች ጥናትና ስርፀት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ አየለ ደምሴ ስልጠናውን ሲሰጡ አስረድተዋል፡፡

ሠራተኞችም በአዋጁ ዝርዝር ህጎችን በመረዳት ከስራ ምዘና፣ ምልመላና መረጣ፣ ቅጥር ደረጃ እድገት፣ የስራ ልምድ ፣ውክልና፣ የአመት ፈቃድ፣ ማስታወቂያ አወጣጥ፣ ሰራተኞች መብትና ግዴታ ዙሪያ ሀሳቦች እና ጥያቄዎችን አንስተው በተጋባዥ ሙያተኛው ሠፊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

በእለቱ ቅጥርና ምልመላን፣ የደረጃ እድገትን፣ ዝውውርን፣ በተጠባባቂነት ማሰራትን እንዲሁም ማትጊያና ማበረታቻን የተመለከቱ ገለጻዎች እና ለጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱ የሰው ሀብት ዳይክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል አሊ ይህንን ደንብ በአግባቡ ስራ ላይ የማዋል ኃላፊነት እንዳለበትና ሰራተኛውም ደንቡን በመከተል ኢንስቲትዩቱን በራዕዩ ያስቀመጠውን ምርጥ ተቋም የመሆን ግብ እንዲያሳካ የራሱን ሚና መጫወት እንደሚ ጠበቅበት ገልጸዋል::

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti