የኢንስቲትዩቱ ሳተላይት ተቋማት የ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የስራ አፈፃጸም አስመልክቶ በሚታዩ ቸግሮች እና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ውይይት ተድርጓል። የውይይቱ ዋነኛ ዓላማ የሳተላይት ተቋማቱ ለትምህረት ጥራት እያከናወኗቸው ያሉ ተግባራት ዙሪያ እርስ በእርሳቸው የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ የሚያግዝ ነው ተብሏል።

Federal TVET Institute

March 3, 2020

በውይይት መድረኩ ላይ የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ የሳተላይት ተቋማት ሀላፊዎች በተቋማቸው የሚታየውን የትምህርት ጥራት ቸግር ለመቅረፍ ሀገራዊ የእውቀት እሴቶችን መጠቀም ተገቢ መሆኑም አንስተዋል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ነባራዊ ሁኔታን በማገናዘብ፣ ህብረተሰቡን ማሳተፍ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልምዶችንና ተሞክሮዎችን መከተል ይገባቸዋል ብለዋል አቅራቢዎቹ።

በእለቱ በግማሽ ዓመቱ አፈፃፀም በድክመት ከተነሱት ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የቋሚ መምህራንና ተመራማሪዎችን በሚፈለገው መጠን በገበያ ላይ አለማግኘት፣ አንዳንድ የትርፍ ሰዓት ተከፋይ የሆኑ መምህራን የቆይታ ጊዜያቸውን ለማራዘም ባልተገባ መንገድ ለተማሪዎችን ውጤት መስጠት፣ የመምህራን ደሞዝ አነስተኛ መሆን፣ከግብዓት አቅርቦት ጋር የተያያዙ ችግሮች፣ የቤተ - ሙከራ አደረጃጀትና የምርምር ላቦራቶሪ ግንባታና ማስፋፊያ ግንባታ መዘግየት፣ ማኅበረሰቡን ተደራሽ የሚያደርጉ ምርምሮችን በሚፈለገው መጠን ያለመከናወን መኖራቸው ተገልጸዋል፡፡

በእለቱ በመድረኩ ላይ የኢንስቲትዩቱ አካዳሚክ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብቶም ገ/እግዚአብሔር ተገኝተው በተነሱ ችግሮች ላይ በሰጡት ምላሽ እንደገለጹት በአዲሱ ፍኖተ ካርታ መሰረት የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች የሚወስዱት የኮመን ኮርሶች ቁጥር ብዛት ያላቸው በመሆኑ ተቋማቱ በአቅራቢያቸው ከሚገኙ ዩንቨርስቲዎች የትርፍ ሰዓት ተከፋይ መምህራንን መቅጠር አማራጭ መሆኑን ጠቅሰው ሆኖም አንዳንድ የትርፍ ሰዓት ተከፋይ የሆኑ መምህራን የቆይታ ጊዜያቸውን ለማራዘም ሲሉ የሚያደርጉት ያልተገባ ድርጊቶች በተመለከተ የዲፓርትመንት ሀላፊዎች የመምህራኑን የስራ አፈጻጸማቸውን በመከታተል ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በሜጀር ኮርሶችን የሚያስተምሩ መምህራንን ቅጥር በተመለከተ ያሉትን ክፍት መደቦች እያየን ቅጥር እንፈጽማለን ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል የተማሪዎች የመመረቂያ ፕሮጀክት መስሪያና የትርፍ ሰዓት ተከፋይ መምህራን የሰዓት ክፍያ በተመለከተ በሁለተኛው ወሰነ-ትምህርት መጀመሪያ ላይ አንደሚለቀቅ ገልጸዋል፡፡ የማህበረሰቡን ችግሮችን ለመፍታት በየተቋማቱ የሚካሄዱ ጥናቶች ላይ ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡

የሳተላይት ተቋማት ብዛት ያለውን ተማሪዎችን አስተምሮ ማስመረቅ ሳይሆን ባሉት የስልጠና ዘርፎች ላይ ውጤታማ ስራን ሰርቶ ተወዳዳሪ ተማሪዎችን መፍጠር ላይ ማተኮር ይገባል ያሉት አቶ ሀብቶም ከመምህራን የደመወዝ ጭማሪ ጋር በተያያዘ በጥናት ተመስርቶ በቀጣይ የሚተገበረው የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ተግባራዊ ሲሆን የሚመለስ ይሆናል ብለዋል፡፡

የሳተላይት አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ በእለቱ ባደረጉት የማጠቃለያ ንግግር የውይይቱ ዓላማ የግማሽ አመት ስራ አፈጻጸም ግምገማ ከማድረግ ባሻገር የሳተላይት ተቋማቱ ለትምህረት ጥራት እያከናወኗቸው ያሉ ተግባራት እና ተሞክሮዎቻቸው ዙሪያ እርስ በእርሳቸው የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ የሚያግዝ ነው ብለዋል ፡፡
አስተዳደር፣ በጀትና ግብአት አስመልክቶ የኢንስቲትቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደምሰው በየነ ፣የዋና ዳሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ክፍሌ እና የእቅድና በጀት ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ መታሰቢያ ተገኝተው በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti