ከኦሮሚያ ክልል ለመጡ የፖሊቴክኒክና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መምህራኖች የማስተማር ስነ-ዘዴ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡ ስልጠናው ስልታዊ የማስተማር ዘዴ መጠቀም የሚችሉ ቁርጠኛና ብቃት ያላቸውን መምህራኖችን ለመፍጠር ያለመ ነው ፡፡

Federal TVET Institute

January 28, 2020

መምህራኖችን ውጤታማ የሚያደርጉ የማስተማር ክህሎቶችን የሚያዳብር ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ አንፃር የትምህርት ዕቅድ እና ቁልፍ ደረጃዎቹ፣ የራሳቸውንና የተማሪዎቻቸውን አቅም ለመገንባት አጋዥ ማቴሪያሎችን በጥራት ማዘጋጀት፤ ስርአተ ትምህርት መቅረጽ እና ማስተካከል፣የተግባቦት መርሆች ላይ ያተኮረ ነው፡፡

የአካዳሚክ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሀፍቶም ገ/እግዚአብሔር በስልጠናው መዝጊያ ስነ-ስርአት ላይ ባደረጉት ንግግር በመልካም የዜግነት እሴቶች የታነፀ ማሕበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት የሚችል በሳይንሳዊ ዕውቀትና አስተሳሰብ የተገነባ ዜጋ ለማፍራት የመምህራን ሀላፊነት ላቅ ያለ በመሆኑ ኢንስቲትዩቱ ለመምህራን ተጨማሪ አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት ተልእኮውን እየተወጣ ይገኛል፡፡

ይህን ተከትሎ ስልጠናው የትምህርት ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችንና መርሃግብሮችን ይበልጥ በመረዳትና የማስተማር ስነ-ዘዴን በመጠቀም በቀጣይ በስራ ገበታቸው ላይ ማህበራዊ ሃለፊነታቸውንና የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ትልቅ እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮ አቅም ግንባታ ሀላፊ ወ/ሮ ታገሰይ ገመቹ እንደገለጹት ቢሮዉ ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በመሆንለመምህራኖቹ ተስማሚ የመማር ማስተማር ሁኔታ መፍጠር፣ በትምህርት ተቋማት ውስጥ ጠንካራ የሕብረተሰብ ግንኙነት እንዲፈጠር የተግባቦት ስልጠናዎችን መስጠት ፣ ጥሩ የውድድር ባሕልን ማዳበር፣ በመምህራን ውስጥ ተከታታይ የስራ መሻሻል ስሜትን ማጐልበት፣ ፣ የአቅም ክፍተት በመለየት ስልጠና ማዘጋጀት ፣ የማስተማር አጋዥ መፃሕፍትን በማዘጋጀት ሥራ የሚጠበቅበትን እንገሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

ስድሳ ሁለቱም ሰልጣኞች ለ10 ተከታታይ ቀናት የማስተማር ስነ-ዘዴ ላይ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን የምስክር ወረቀት ከኢንስቲትዩቱ ተሰጥቷቸዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti