በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የክህሎት ውድድር 20 የሚሆኑ ሙያዎችን በመለየት የመወዳደሪያ ፓኬጅ እየተዘጋጀ ነው::
የክህሎት ማወዳደሪያ ፓኬጁን የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ፣ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩቱ፣የክልሎችና የፖሊቴክኒክ ተቋማት እንዲሁም የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች እያዘጋጁት ነው፡፡

Federal TVET Institute

January 15, 2019

የቴክኖሎጂ መቅዳት፣ ማላመድ ፣ማስተላለፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አያሌው ሳህሌ እንደተናገሩት የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ እና ኢንስቲትዩቱ የሚያዘጋጁት 2ተኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ፣የስልጠና ጥራትን ማሻሻልና በአሰልጣኝ፣ በሰልጣኞችና በአንቀሳቃሽ ኢንተርፕራይዞች ዘንድ የውድድር ተነሳሽነትን በመፍጠር ስራ ፈጣሪነትን እንዲሁም በኢንዱስትሪው የምርት ተወዳዳሪነትን ማሳደግ እጅጉን ያግዛል።

በ2011ዓ.ም በ 9 የተመረጡ ሙያዎች ላይ አሰልጣኞችና ሰልጣኖችን የክህሎት ማወዳደሪያ ፓኬጅ በማዘጋጀት ውድድሩ ተከናውኖ የነበረ ሲሆን በዘንድሮ የበጀት ዓመት እቅድ፤ ከየተቋማቱ ተልእኮ አንጻር አዳዲስ የትኩረት አቅጣጫዎችና (thematic areas) ተጨማሪ ለተመረጡ 11 ሙያዎች በድምሩ 20 ፕሮጀክቶች ተለይተው ለውድድሩ የሚሆን ፓኬጅ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የስልጠና ቡድን አስተባባሪ አቶ ይታየው ደሊል እንደገለጹት የማወዳደሪያ መሳሪያ/ፕሮጀክት በዚህ መርሀ ግብር ከማዘጋጀት በተጨማሪ የሙከራ ትግበራ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሙያው በተዘጋጁ ወርክ ሾፖች ላይ እንደሚከናወን የገለጹ ሲሆን ክፍተት ያለባቸውን ፕሮጀክቶችም ከውድድሩ አስቀድሞ ማስተካከያ ይደረጋል ፡፡

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ማዕቀፍን መነሻ የሚያደርገው የክህሎት ውድድር ፕሮግራም ደረጃ 3 የሙያ ደረጃ ላይ ያሉትን ተወዳዳሪዎች ወስዶ አለም አቀፍ ተሞክሮ በመቀመር በተመረጡ የሙያ አሀዶች መነሻነት ለሚሰሩ የፕሮጀክት ስራዎች የዲዛይን ፣ የኢንፎርሜሽን ፣ የድሮዊንግና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን መረጃዎች በመስጠት ተወዳዳሪዎችን በነጥብ ይገመግማል።

የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች የክህሎት ውድድር ከተቋማቱ ተልእኮ አንጻር (thematic areas) የተመረጡ 10 ሙያዎች ተለይተዋል ብለዋል፡፡

የክህሎት ማወዳደሪያ ፓኬጆች በማዘጋጀት ላይ የሚገኙት የኤጀንሲው፣ የኢንስቲትዩተ፣የክልሎችና የፖሊቴክኒክ ተቋማት እንዲሁም የሚመለከታቸው የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች በያዝነው ሳምንት መጨረሻ ላይ ያጠቃልላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti