‹‹ተግባራዊ ስልጠና የተማሪዎችን በራስ መተማመን ያጎለብታል››

Federal TVET Institute

January 1, 2020

ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከመካኒካል እና ኢንዱስትሪያል ትምህርት ክፍሎች በቁጥር አንድ መቶ ሐምሳ የሚሆኑ የ5ኛ ዓመት ተማሪዎች በኢንስቲትዩታችን ማኑፋክቸሪንግ ትምህርት ክፍል የተግባር ስልጠና ላይ ይገኛሉ፡፡

‹‹የተለያዩ ተቋማትን በማወዳደር በተሻለ ሁኔታ በስልጠና ቁሳቁሶች የተደራጀ ሆኖ በማግኘታችን የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩትን መርጠን ተማሪዎችን አምጥተናል›› ያሉን መምህር ካሱ ናቸው፡፡

‹‹የንድፈ-ሀሳብ ስልጠና እያስተማርኩ ተግባራዊ ስልጠና ማሳያ ክፍል ሳጣ ይሰማኛል›› የሚሉት መምህር ካሱ የኢንስቲትዩቱን የተደራጁ የስልጠና ክፍሎች በማየታቸው ደስተኛ እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡

በስልጠና ላይ ያገኘናቸው ተማሪዎች በኢንስቲትዩቱ ደስተኛ መሆናቸውን ነው የሚናገሩት፡፡ ከተማሪዎች መካከል አብረሀም ሀጎስ ከዚህ ቀደም ሌሎች ተቋማት ሔዶ ስልጠና መውሰዱን አስታውሶ በስልጠና ቁሳቁስ፣ በአሰልጣኞች ብቃት፣ ከስልጠና አሰጣጡ አኳያ ኢንስቲትዩቱ የተሸለ ሆኖ እንዳገኘው ይናገራል፡፡
‹‹ለምሳሌ ሌዝ ማሽን (Lathe Machine) በመሰልጣኔ ደስተኛ ነኝ፡፡ በግልም ሆነ በቡድን ብንሰራበት ትልቅ ጥቅም የምናገኝበት ስልጠና ነው፡፡›› በማለት ይናገራል፡፡

‹‹እንዲህ ያሉ ስልጠናዎች መሰጠታቸው ተማሪዎች በራስ መተማመናቸውን ያዳብራሉ፣ በስራ ላይ ሲሰማሩም ውጤታማ ይሆናሉ፤ ሀገራችም በእነሱ የበለጠ ተጠቃሚ ትሆናለች›› በማለት መምህር ካሱ የስልጠናውን አስፈላጊነት ያስገነዝባሉሉ፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti