የጸረ-ሙስና ቀን በኢንስቲትዩቱ ተከበረ

Federal TVET Institute

December 6, 2019

ቀኑን በንግግር የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተሻለ በሬቻ ሲሆኑ በንግግራቸውም የስነምግባርና ጸረ-ሙስና ቀንን በየአመቱ ስናከብር በአለማችን ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ ችግር እየሆነ በመምጣቱ ፤ ችግሩን ለመቅረፍና መከላከል እንዲንችል ህብረተሰቡን የግንዛቤ መስጠት አስፈላጊነቱ የጎላ በመሆኑ እንደሆ ተናግረዋል፡፡

የስነ-ምግባር ጉዳይ ትውልዱና ሀገርን የማዳን ጉዳይ በመሆኑ ሀሉም ሰው በመልካም ስነ ምግባር አርአያ በመሆን ትውልድና ሀገርን የመታደግ ሥራ መስራት እንደሚገባ የገለጹት አቶ ተሻለ በሬቻ እለቱን ማሰብ ጥሩና ወቅታዊ መሆኑን አንክሮት ሰጥተው ሁሉም ራሰን ተጠያቂ የማድረግ ጉዳይ ላይ ማተኮር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ሙስናን በተመለከተ የተቋሙን ሃብትና ንብረት በአግባቡ በመጠቀምና ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ ሙያዊ ስነ- ምግባርን በጠበቀ መልኩ ሁሉም ሰራተኞች ኃላፊነታቸውን በመወጣት ለሃገር ልማትና ዕድገት የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በእለቱም የመወያያ ሰነድ የቀረበ ሲሆን ስለ ሙስና ምንነት፣ መገለጫዎች፣ መከላከያ መንገዶችና የሙስና ወንጀል ህጎች፣ የሙስና ሃገራዊና አለምአቀፋዊ ገጽታዎች፣በስነ ምግባር እና ሙስና ጽንሰ ሀሳብ፣ በስነ-ምግባር አስፈላጊነትና ሊዳብሩ በሚገባቸው እሴቶች፤ በሙስና መንስኤ፣ ጉዳትና መከላከያ ስልቶች እንዲሁም በሙያዊ ስነ- ምግባር ላይ ያተኮረ ገለፃ የኢንስቲትዩቱ የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ወ/ጊዮርጊስ ባልቻ አቅርበዋል፡፡
የሙስና አፈፃፀም ስልት ለሙስና የሚያመች ህግን በማውጣት የነበሩትን ህጎች በማላላት ሃላፊነት በጎደለው መንገድ ከተጠያቂነት ለመዳን የሚደረጉ ተግባራት እየተስተዋሉ መሄዳቸው ለሙስናና ብልሹ አሰራሮች መስፋፋት እንደ ምክንያት እንደሚጠቀሱ አብራርተዋል፡፡

ሙስናን ለመከላከል ለአንድ ክፍል ብቻ የተሰጠ ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን በየተቋሙ ያሉ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ሙስናን ለመከላከል ቆራጥና አሰራሮችን የመፈተሸና የመከታተል እንዲሁም የውስጥ ኦዲት ቁጥጥርን ማጠናከር አለባቸውም ብለዋል፡፡

ብልሹ ስነ ምግባርንና ሙስናን የመዋጋቱ ስራ በተቋማዊ አደረጃጀት ብቻ የሚሳካ ባለመሆኑም ሰራተኞች እና የሚመለከታቸው አካላትን የተቀናጀ ተሳትፎ ለማሳደግ መስራት እንደሚገባ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti