በብየዳ ሙያ ላይ ብቃት ያላቸውን የሰው ሀይል ለማፍራት ቅንጅታዊ አሰራር ስርአትን ማጠናከር ይገባል ተባለ፡፡

Federal TVET Institute

December 5, 2019

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት የብየዳ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ማዕከል የ2012 በጀት አመት ከክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ፣ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች እና ከቴክኖሎጂ የብየዳ ማእከላት ሀላፊዎች ጋር የጋራ እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር እየገባ ነው፡፡

የኢንስቲትየቱ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ም/ዋና ዳሬክተር አቶ እንየው ጌትነት እንደገለጹት በሀገራችን የግብርና መር ኢኮኖሚውን በኢንዱሰትሪ መር ለመተካት በምታደርገው ጥረት በማኑፋክቸሪንግ የልማት ዘርፍ ላይ ያተኮረ የቴክኖሎጂ ልማት ስትራቴጂን መተግበር ወሳኝ ድርሻ አለው ፡፡
የብየዳ ስልጠና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆንና አገራችን የያዘቻቸውን ሜጋ ፕሮጀክቶች የሀገር ዉስጥ ባለሙያ ገብቶ የመፈፀም አቅም እንዲኖር በሙያው ብቁ የሆኑ የሰው ሃይል በማፍራት ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው ብለዋል ፡፡
በዚህም የባለሙያውን አቅም እና ክህሎትን በማሳደግ ቴክኖሎጂዎችን የመቅዳት፣የማሸጋገር ሂደት ላይ ኢንዱስትሪውን መመገብ እንዲቻል ኢንስቲትዩቱ የብየዳ ቴክኖሎጂ አስመልክቶ ክልሎች ጋር በጋራ እቅድ አውጥቶ በቅንጅት መስራቱ ጉልህ አስተዋትኦ እንደአለው ገልጸዋል፡፡
የማእከሉ የብየዳ ቴክኖሎጂ ሀላፊ አቶ ማትዮስ አሸናፊ እንደገለጹት የተዘጋጀውን እቅድ ወደ ታች ከማውረድ ይልቅ በየክልሉ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የጋራ እቅድ በማዘጋጀት በውይይት ግብአት ለማሰባሰብና እቅዱን ለማጎልበት ተችሏል ፡፡
ከደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አበራሽ አለሙ እቅዱን አስመልክቶ እንደገለጹት የብየዳ ቴክኖሎጂን በተደራጀ መልኩ ለመምራት የክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮ እና የስልጠና ተቋማት ኢንስቲትዩቱ ስለብየዳ ቴክኖሎጂ ግንዛቤ ፈጥሮ ባለቤት እንድንሆን እንደክልሉ ነባራዊ ሁኔታ ታቅዷል ፡፡
ቀልጣፋና ውጤታማ የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት፣ በክላስተር በመቀናጀት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መልክ ለመምራትና ለመፈጸም ያስችለናል ብለዋል፡፡
የብየዳና ቴክኖሎጂ ማእከል የቴክኖሎጂ ዳይሬክተር አቶ ፋንታሁን እንደገለጹት በአለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊ በያጆችን ለማፍራት ከባለድርሻ አካላት ጋር የደረስንበት መግባባት በአጭር ጊዜ ብዙ ዉጠየት ለማስመዝገብ ይረዳል፡፡

ስለማእከሉ የስራ እንቅስቃሴ በሌላ ዘገባ ሰፋ አድርገን እናስቃኛችኋለን፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti