ኢንስቲትዪቱ የጥራት ስራ አመራር(ISO) ሰርተፍኬት ለማግኘት እየሰራ ነው:: ለዚሁ አላማ የተዋቀረው ግብረ-ሀይል የውስጥ ኦዲት በማድረግ ላይ ነው፡፡

Federal TVET Institute

November 27, 2019

የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዋና ዳሬክተር አቶ እንየው ጌትነት እንደገለጹት ( Quality Management system) ወይም ISO 9001:2015 የISO 9001፡2015 የጥራት ሥራ አመራር ስርዓትን ለመተግበር ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ጋር ኢንስቲትዩቱ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ኢንስቲትዩቱ ለዚሁ አላማ ያቋቋመው 12 አባላት ያሉት ግብረ-ሃይል የጥራት ሥራ አመራር ስርዓትን ለመተግበር የሚያስችሉ የአሠራር መመሪያዎችን በማዘጋጀት፣ ስልጠና እንዲወስዱ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በማዘመን አለማቀፍ ተወዳዳሪ የመሆን ራዕዩን ለማሳካት እውቅና ያለውን የጥራት ሥራ አመራር ስርዓትን ለመተግበር ግብረ -ሀይሉ የውስጥ ኦዲት እንዲያደረግ መመሪያ ሰጥተዋል ፡፡

የኢንስቲትዩቱ የትምህርት ጥራት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና የግብረ-ሀይል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ወሉ ሓጎስ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ የተቋቋመበትን ዓላማና ተልዕኮ ባገናዘበ ሁኔታ የተለያዩ ዓለም አቀፍና ሀገራዊ ስምምነትና ህገ ደንቦችን በማመሳከር የጥራት ስራ አመራር (Quality Management System) ማኑዋል በመቅረፅ ወደ ተግባር መግባቱን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ደንበኞች ላይ ያተኮረ የአሠራር ስርዓት መዘርጋት፣ አመራር ሰጪነት ጠንካራ የአመራር ስርዓት መተግበር፣ ሠራተኞችን በስርዓቱ እና በአግባቡ በመምራት በማሰማራት እንዲሁም በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ የISO 9001፡2015 መሰረታዊ መርሆዎችን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ግብረ ሀይል በ4ቱ ዘርፎች፣ በዋና ዳይሬክተር ፣በአካዳሚክ ፣በአስተዳደር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፎች ተጠሪ በሆኑት ላይ የውስጥ ኦዲት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ግብረ ሀይል የጥራት ሥራ አመራር የISO 9001፡2015 ማግኘት በሚያስችለውና ሊሻሻሉ በሚገባቸው የኦዲት ግኝቶች ዙሪያ በቀጣይ ሳምንት ሪፖርት ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti