የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር በተመለከተ ለኢንስቲትቱ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ ስልጠናው ሰራተኞችን የፋይናንስ ደንብ ፣ አዋጅ ፣ ህግና መመሪያዎችን አውቀው እንዲከተሉ የሚስችል ነው ተብሏል፡፡

Federal TVET Institute

November 4, 2019

የኢንስቲትቱ የፋይናንስ ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀብተወለወድ ሀይሉ እንደገለጹት የዚህ ስልጠና ተቀዳሚ ዓላማ ለሰራተኞች የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ስርአት በተመለከተ አቅም መገንባት እንደሆነና ቀልጣፋ ፤ውጤታማ ፤ግልጽ፤ ተጠያቂነትና ፍትሃዊ ተደራሺነት ያለው አገልግሎት እንዲኖር ማስቻል ነው፡፡

ስራን በታቀደው ጊዜ ለማከናወን ፋይናንስ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት አቶ ሀብተ ወልድ ስራዎችን በእውቀት ተመስርቶ ለማከናወን የሚቻልበትን መንገድ ክፍተታቸውን እንዲያውቁ አስቸላቸዋል ብለዋል፡፡

ስልጠናው ለከፍተኛ ባለሙያዎችና አመራሮች የመንግስት ፋይናንስ ሥርዓቱ የሚመራባቸው አዋጅና መመሪያዎች ላይ ግንዛቤ ከማሳደግ አኳያ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት ከገንዘብ ሚኒስቴር አቶ በየነ ገረመው ሲሆኑ የመንግስት ሂሳብ አሰራር መሰረቶች፤ የፋይናንስ ደንብ፣ አዋጅ፣ ህግና መመሪያዎችን የሂሳብ ሪፖርት ይዘትና የማቅረቢያ ጊዜ እንዲሁም የፌደራል መንግስት የፋይናንስ ተግባርና ኃላፊነት ላይ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ሰጥተዋል፡፡

በስልጠናውም የኢንስቲትቱ ዳይሬክተሮች፣ የትምህርት ክፍሎችና ፋካሊቲዎች ኃላፊዎች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ከዳይሬክቶሬቱ ጋር ያለውን ተግባቦት ለማስተካከል አመቺ ሁኔታ የሚፈጥር ነው በዚህም ስልጠና ጥሩ የሚባል ልምድ የወሰድንበትና የአሰራር ተሞከሮ የተጋራንበት ነበር ብለዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti