የኢንስቲትዩቱ ግዢና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ሰራተኞች ላይ የሚታየውን አመለካከት እና የክህሎት ችግር ለመቅረፍ ስልጠና ሰጠ፡፡ የኢንስቲትቱ ዳይሬክተሮች፣ የትምህርት ክፍሎችና ፋካሊቲዎች ኃላፊዎች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች በስልጠናው ተሳትፈዋል፡፡

Federal TVET Institute

November 3, 2019

የኢንስቲትቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደምሰው በየነ በስልጠናው መክፈቻ ወቅት ባደረጉት ንግግር ሰራተኞች የግዢ ንብረት አስተዳደር የሚመራበት መመሪያ ካለማወቅ የአሰራር ግድፈቶች ይስዋላሉ ፡፡

አብዛኛው ሰራተኛ እንዴትና በምን አግባብ ግዢ መጠየቅ እንዳለበት ካለማወቅ በርካታ ቅሬታዎችና አለመግባባቶች እየተከሰቱ መሆኑን የገለጹት አቶ ደምሰው ይህ አይነቱን አመለካከትና የክህሎት ችግር ለመቅረፍ ለሚመለከታቸው አካላት ዳይሬክቶሬቱ ስልጠና እድል ማመቻቸቱን ገልጸዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ኦዲተር አቶ ገበያው ጉዳይ ሲሆኑ የግዢና ንብረት አስተዳደር ተግባርና ሀላፊነት ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ስራን በተገቢው ሁኔታ ለማሳለጥ ግዢ በአግባቡ እና በወቅቱ መፈጸም እንዳለበት የሚያግዝ የግዢ አሰራር ስርአት ላይ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ሰጥተዋል፡፡

ስልጠናውን ተሳታፊ ከሆኑት መካከል የኢንስቲትዩቱ የለውጥ እና መልካም አስተዳደር ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀይለ መስቀል ተሾመ ስልጠናውን በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ስልጠናው በዓመቱ መጀመሪያ አካባቢ መሰጠቱ ወቅታዊነቱን የጠበቀ ነው ፡፡
ከዚህ ቀደም ህጎቹን ባለመረዳት ለስራ ማስኬጃ የሆኑ ግብአቶችን እንዴት እና በምን መመሪያ መሰረት መጠየቅ እንዳለብን የእውቀት ክፍተቶች ነበሩብን ያሉት አቶ ሀይለ መስቀል ከልጠናው በቂ እውቀትና ግንዛቤ እንዳገኙበት ገልጸዋል፡፡

አቶ ሀይለ መስቀል በቀጣይ IFMS ስልጠና እንዲሰጥ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

በቅርቡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ ለአመራሮችና ለሰራተኞች IFMS በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንደሚሰጥ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክሬት ዳይሬክተር አቶ ደምሰው ተናግረዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti