በሻሻለው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የስነ-ምግባር መመሪያ ለአዳዲስ ተማሪዎች ገለጻ ተደረገ፡፡ ከኢንስቲትቱ የተለያዩ ክፍሎች የተውጣጡ አመራሮች ለአዳዲስ ተማሪዎች ኦረንቴሽን ሰጥተዋል

Federal TVET Institute

November 3, 2019

ኢንስቲትዩቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ12ተኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎችን በዲግሪ መርሀ ግብር ለማስተማር መቀበሉን ተከትሎ በዋናው ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አድርጓል፡፡

በእለቱ በዲግሪ መርሀ ግብር ለመማር ከሀገሪቱ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች የተውጣጡ አዳዲስ የc ድረጃ አሰልጣኞችና የድህረ ምረቃ ተማሪዎችም ተገኝተዋል፡፡

በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የተማሪዎች ዲን ሀላፊ አቶ ወንድይራድ በሀይሉ አዲስ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ኢንስቲትዩቱ በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ የልህቀት ማእከል ለመሆን ራዕይ አስቀምጦ እየሰራ ያለ ትልቅ ተቋም መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም እንደማሳያ በሀገራችን በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ መርሀ ግብር የሚያሰለጥን ብቸኛ ተቋም ነው ብለዋል
በተለይ በአሁኑ ጊዜ አለም ወደ አንድ መንደር እየመጣች ባለችበት ሰዓት በዘርና በቋንቋ ከሚከፋፍሉ እኩይ ባህሪ ካላቸው ግለሰቦች እራሳቸውን በመጠበቅ ለቤተሰብ እንዲሁም ለሀገር የሚበጅ እውቀት ይዘው እንዲወጡ መክረዋል፡፡

የመማር ማስተማሩ ሂደት የሚያደናቅፍ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይኖር ከየካ ክ/ከተማ ከላምበረት አካባቢ ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል
የስነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወ/ርጊዮርጊስ ባልቻ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተላከ የስነ-ምግባር መመሪያ፣ በሬጅስትራር ህጎች፤ እና በአዲሱ የትምህርት ሥርዓት በተመለከተ ሰፋ ያለ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ተማሪዎቹም በቆይታቸው መብትና ግዴታቸውን አውቀው በማይተገብሩ ተማሪዎች ላይ በመመሪያው መሰረት እንደሚቀጡ አሳስበዋል፡፡

የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብይ ድፋባቸው ኢንስቲትዩቱ ለተማሪዎች በግቢ ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ በሚያገኟቸው የምግብ፣ የመኝታ፣ የውሃ፣ የመብራት፣ የመዝናኛ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን በበቂ ሁኔታ አሟልቶ ለተማሪዎች ለማቅረብ ጥረት ሲደርግ መቆየቱን ጠቅሰው ማንኛውም ተማሪ በምንሰጣቸው አገልግሎቶት የጥራት ጉድለት ቢኖር እንኳን በመነጋገር ችግሮችን እንደሚፈቱ የተናገሩት አቶ አብይ ይህንን ምክኒያት በማድረግ የተለየ አላማ አንግበው ለሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች መጠቀሚያ እንዳይሆኑና በዋናነት ለመጡበት ዓላማ ትምህርታቸው ላይ ብቻ ማተኮር እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡

በእለቱ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ዳይሬክተሮች፣ መምህራን እና የእለቱ የክብር እንግዶች እጅግ የሚያነቃቃና ራዕያቸውን የሚያሰፋ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የራሳቸውን ልምድ እና ተሞክሮ ተነስተው፤ ትምህርት የማይፈታው ችግር እንደሌለና ካሰቡበት ተማሪዎች ከፍ ያለ ደረጃ መድረስ እንደሚችሉ እና ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውን ፣ሀገራቸውን አልፎ ተርፎም ዓለምን ማስጠራት እንደሚችሉ ለተማሪዎቹ አብራርተዋል፡፡
ተማሪዎቹም በገለፃው እጅግ ደስተኛ የሆኑ ሲሆን ኢንስቲትቱ ላስቀመጠው የስነምግባር ደንብ ተገዢ እንደሚሆኑም ገልፀዋል፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti