የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ የክህሎት የቴክኖሎጂ እና የተግባራዊ ምርምር ውድድር ሲምፖዝም እና በኤግዚብሽን 252ሺህ850 ህዝብ ጎብኝቶታል ተባለ፡፡

Federal TVET Institute

October 29, 2019

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምርትና ስልጠና ኤጀንሲ እና ኢንስቲትዩቱ በጋራ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪው የሆነው የክህሎት የቴክኖሎጂ እና የተግባራዊ ምርምር ውድድር ሲምፖዝየም እና ኤግዚቢሽን የነበሩ ጥንካሬዎችንና ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች እንዲሁም የ2012 እቅድ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት የ2011ዓ.ም ሀገር አቀፍ የክህሎት የቴክኖሎጂ እና የተግባራዊ ምርምር ውድድር ሲምፖዝም እና በኤግዚብሽን የተከናወኑ ስራዎችን አቅርበዋል፡፡

ስራዎቹ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ከሁለቱም ተቋማት የተውጣጡ አብይ፤ ኦፕሬሽናልና ቴክኒክ ኮሚቴዎችን በማደራጀት እቅድ በማቀድ እንድሁም ውድድሩ የሚመራበትን የአሰራር መመሪያዎችን በማዘጋጀትና ለክልሎችና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች ኦረንቴሽንና ስልጠና መሰጠቱ፤

ለክልሎችና ተቋማት በአካል ድጋፍና ክትትል በማድረግ፤ ለውድድሩ አሰፈላጊ ግብአቶችንና በቂ በጀት በመመደብና ውድድሩ በደማቅ ሁኔታ እንዲከናወን በተለይም የቴክኒክና ሙያ ትምርትና ስልጠና ገጽታ ግንባት ለመፍጠር የተደረገዉ ቅድመ ዝግጅት ተግባራት አፈጻጸም አበረታች እንደነበር በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

ለውድድር የቀረቡት 163 ቴክኖሎጂዎች ለህዝብ እይታ የቀረቡ ሲሆን ከጋምቤላ እና ኢትዮሶማሌ ክልሎች ውጪ ሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተሳታፊ ነበሩ፡፡

ለአምስት ቀናት የቆየው ይሀው ሀገር አቀፍ የክህሎት የቴክኖሎጂ እና የተግባራዊ ምርምር ውድድር ሲምፖዝም እና በኤግዚብሽን 252ሺህ850 ህዝብ ጎብኝቶታል ብለዋል፡፡

የኤግዚቢሽኑ የሚገልጹ የህትመት ውጤቶች ውስን በሆነ ቦታ ላይ ለእይታ መቅረቡ፣ ተግባሩ እንደተጠናቀቀ ስራዎችን በወቅቱ አለመገምገም፣ ለውድድር ተሳታፊዎች እንዲሁም ለዳኞችና ድጋፍ ላደረጉ አካላት የምስክር ወረቀት ማሳተም ላይ ክፍተት እንደነበረ ተጠቅሷል፡፡

በመቀጠል የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የክህሎት የቴክኖሎጂ እና የተግባራዊ ምርምር ውድድር ሲምፖዝም እና በኤግዚብሽን እቅድ በአምላክ ታደሰ ቀርቧል

በዘንድሮው ዓመት ለ2ኛ ጊዜ የሚካሔደው ይኸው ውድድር ከመጋቢት ወር አጋማሽ በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናa ኢንስቲትዩት ቅጥር ግቢ ውስጥ በደማቅ ሁኔታ ይከተበራል ተብሏል፡፡
ዉድድሩ የታለመለትን ግብ እንዲመታ የሁለቱም ተቋሞች ከፍተኛ አመራሮች፤ ኦፕሬሽናል እና ቴክኒካል ኮሚቴዎች እንዲሁም ሌሎች አጋዥ ንኡሳን ኮሚቴዎች የተሰጣቸዉን ተግባርና ኃላፊነት ተቀብለዉ ዉጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti