በ 10 የሙያ መስኮች የ ገበያ ጥናት ( Labor market survey) ተደርጓል፡፡
የ ገበያ ጥናት የተካሄደው ከ 2014-2015 ዓ/ም ሲሆን በትምህርት ክፍሎች የሚሰጠው ሥልጠና የገበያውን ፍላጎት ማዕከል ያደረገ ስለመሆኑ እና ሥርዓተ ትምህርቱ በገበያ የሚፈለጉ እውቀትና ክህሎቶች የያዘ ስልመሆኑ ለማወቅና ልዩነትን ለማጣጣም እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች እንደ መረጃ ምንጭነት ይረዳ ዘንድ ነው፡፡
በ 10 የሙያ መስኮች የምሩቃን ዳሰሳ ጥናት (Tracer study) ተደርጓል፡፡
የ 2019-2021 G.C. ምሩቃን ዳሰሳ የተካሄደው በዋነኛነት ከ TI የተመረቁ ምሩቃን በምን ሥራ ላይ ተሠማርተው እንደሚገኙ ለማወቅ፡ ምሩቃን የተማሩት ትምህርት ከሚሠሩት ሥራ ጋር መጣጣሙን ለማወቅ እና በስራ ቦታ ያጋጠማቸውን ፈተና ለማወቅ ታቅዶ ነው፡፡
ከፈረንሳይ ሀገር ለመጡ የፕሮጄክቱ ከፍተኛ አመራሮች የአንድ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦላቸው ውይይት የተደረገ ሲሆን በክትትሉ እና በተደረገው ውይይት አፈፃፀም ጥሩ እንደነበረ ተመስክሮለታል፡፡
የ Peer Learning Networking Manual ተዘጋጅቷል፡፡ ማኑዋሉ የተዘጋጀው መምህራን ከሌላ ዩንቨርሲቲ መምህራን በተለይም ደግሞ ከ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጥምረት መማማር እንዲችሉ እና ያላቸውን እውቀትና ክህሎት እንዲጋሩ ለማስቻል ታስቦ ነው፡፡
የ 2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ድግሪ እጩ ምሩቃንን ለሥራ ዝግጁ ለማድረግ የ ሥራ ዝግጁነት ( Work readiness and career support) ሥልጠና የተዘጋጀ ሲሆን ለመሰልጠን ፈቃደኛ ከሆኑት እጩ ምሩቃን መካከል ለ 156 ቱ የ 2 ቀን ሰልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡
ለ ሁለተኛ ድግሪ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች በምርምር ጽሑፍ አዘገጃጀት እና አቀራረብ ላይ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን እና ተመራማሪዎች በተለያየ ርዕስ ላይ የተዘጋጀ የምርምር ውጤት ገለፃ የተደረገ ሲሆን ተማሪዎች ልምድ እንዲቀስሙ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮላቸዋል፡፡
በተቋሙ የገበያ ፍላጎትን ያማከለ ሥርዓተ ትምህርት ለመቅረፅ የሚረዳ የ Curriculum framework በመዘጋጀት የምስጥ ግምገማ በማካሄድ በተሰጡት ማሻሻያ ሀሳቦች እርማት ተደርጎበት ለወጭ ገምጋሚዎች እንዲቀርብ ቀን ተቆርጦለታል፡፡