3ኛው ዓመታዊ የመካኒካል ቴክኖሎጂ ፋካሊቲ ጥናትና ምርምር ሴሚናር ዘመኑ በሚጠይቃቸው እድገቶች እና ለውጦች ላይ ለመምከር #Recent_Advances_in_Automotive_and_Manufacturing_Technology/ Engineering በሚል ርዕስ መካሄድ ጀመረ። ******************ግንቦት 26/2016***********

የኢንስቲትዩቱ የጥናት ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ሐብታሙ_ሙሉጌታ ሴሚናሩን በንግግር ሲከፍቱ ኢንስቲትዩቱ በየሳምንቱ ጥናትና ምርምር ሴሚናር እያካሄደ 29ኛ ሳምንት መድረሱን ገልጸው ፋካሊቲዎች የጥናት ምርምር ዳይሬክቶሬት ጋር በመቀናጀት ከኢንስቲትዩቱ ባለፈ በአገሪቱ በየዘርፋቸው ያሉ ምሁራንን እያሳተፉ ሴሚናር እያካሔዱ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
እንደዚህ ያሉ ሴሚናሮች ምሁራን ልምድ በመለዋወጥም ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ክህሎት ለመጨበጥ ያስችላል ብለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጥራት ያለው ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ለማምረት ምቹ መደላድል እንደሚፈጥር ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የሆኑት ደ/ር #ደረጀ_እንግዳ ባስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት በአውቶሞቲቭ እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ዓለም በከፍተኛ ሁኔታ እየተለወጠ መሆኑን ገልጸው ስልጠናዎቻችን በዚህ ልክ የተቃኙ፣ ጥናትና ምርምሮቻችን ዘመኑ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ ለመፍጠር የሚያስችሉ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡
ከጥናትና ምርምር ዝግጅት አኳያ የሚጠኑ ጥናቶች ያላቸው ደረጃ መፈተሽ እና የየጊዜው እያደጉ መምጣት አልባቸው ያሉት ዶ/ር ደረጀ በየዘርፉ የምናሰለጥናቸው ሰልጣኞች የዛሬን ብቻ ሳይሆን የወደፊቱን የገበያ ፍላጎት የሚመልስ ክህሎት የሚጨብጡ መሆን ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
በሴሚናሩ ስድስት ጥናትና ምርምር ወረቀቶች እንደሚቀርቡ የገለጸ ሲሆን እነሱም አቶ #አዲስዓለም_አደፍርስ (ከዲላ ዩኒቨርሲቲ) Design and Manufacturing of Manually Operated Multiple-seed Planting Machine፣ ዶ/ር #አበራ_እንዳሻ (ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ) Study of Drill Hole Surface of Enset/Sisal Hybrid Composite Material፣ #ፔሩማላ_ጃናኪ (ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት) Manufacturing excellence through Industry 4.0 technologies – an overview፣ #ሰባሻ_ቻንድራ (ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት) Modelling and analyzing the Deep Drawing Process using ABAQUS Explicit and design of expert (DOE) for low cost production of house hold aluminum flat pot፣ አቶ #ቴዎድሮስ_ኪዴ (ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት) Assessment of blended vegetable oil (Jatropha Curcas L and Cottonseed oil) on the tribological properties of bio-፣ አቶ #ሐይለገብርኤል_ዘወዴ (ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ) Experimental investigation on impacts of castor seed oil additives on performance and emissions of diesel engines የሚሉ እንደሆኑ ከፕሮግራሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በዚህ የአንድ ቀን ሴሚናር ላይ ፓናል ውየይት እና ጉብኝት ይካሔዳል፡፡