ሥርዓተ ትምህርቱ ሰልጣኞችን ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ብቁ አድርጎ ያዘጋጃቸዋል ተባለ፡፡

Federal TVET Institute

August 5, 2019

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት የድህረምረቃ ት/ቤት የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ክለሳ ያካሔደው ባለፈው ሳምንት በቢሾፍቱ ነበር፡፡ 

የኢንስቲትዩቱ የአካዳሚክ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብቶም ገ/እግዚአብሔር የስርዓተ ትምህርቱን ዝግጅት እና ክለሳ መነሻ ሲያብራሩ “አንድ ካሪኩለም ተዘጋጅቶ ተማሪ ካስመረቀ በኋላ ዳሰሳ ጥናት ይካሔዳል፡፡ እኛም ጥናት አካሒደን በተለይም የማስተርስ ዲግሪ (A level) ተማሪዎች በስትራቴጂው የተቀመጠውን የቴክኖሎጂ ማሸጋገር ከማሳካት አንጻር ክፍተት እንዳለባቸው ለይተናል፡፡ ይህንን ክፍተት ለመሙላት በማቀድ ነው ያካሔድነው” ብለዋል፡፡ በመሆኑም አዲሱ ስርዓተትምህርት ሰልጣኞች ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ብቁ አድርጎ እንደሚያዘጋጃቸው ተናግረዋል፡፡

በዚህ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት እና ክለሳ ላይ በነባር ስምንት እና በአዲስ ሁለት ትምህርት ክፍሎች ተካትተዋል፡፡ እነሱም Wood works technology mgt, Construction Technology mgt, ICT, Communication tech mgt, Control tech mgt, Automotive Technology mgt, Manufacturing Technology mgt እና TVET Leadership and Management በነባር ክለሳ የተካሔደላቸው ሲሆኑ Textile technology እና Garment technology የትምህርት ክፍሎች ደግሞ በአዲስ ዝግጅት የተካሔደላቸው ናቸው፡፡

በተለይም ለአዳዲሶቹ ዝግጅትን በተመለከተ አቶ ሀብቶም “በአገራችን ላሉ ወጣቶች ከፍተኛ የስራ እድል ከሚፈጥሩ ዘርፎች መካከል ጋርመንት ቴክኖሎጂ እና ቴክስታይል ቴክኖሎጂ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በመሆኑም ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን የሰው ሀይል ለገበያው ለማፍራት የሚሰሩ ኮሌጆች ላይ የሚያስተምሩ የB level (የመመሪያ ዲግሪ) እና A level (የሁለተኛ ዲግሪ) አሰልጣኞችን ማፍራት በማስፈለጉ ነው” ብለዋል፡፡

በኢንስቲትዩቱ በ2011 አካዳሚያዊ ህግጋት (Academic Legislation) የመከለስ ስራ የተሰራ ሲሆን በዚህም 48Credit Hour ወደ 40Credit Hour የማውረድ ስራ ተሰርቷል፡፡ ስለዚህም የትምርት አይነቶችን መምረጥ ግዴታ መሆኑ ሌላኛው ለስርዓተ ትምህርት ዝግጅት እና ክለሳ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ የተሳተፉ የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞች እና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችእና የምርምር ተቋማት የተጋበዙ ምሁራን ስለአበርክቷቸው ከአካዳሚክ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተሩ እጅ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተረክበዋል፡፡
አዲሱ የድህረምረቃ ት/ቤት ስርዓተ ትምህርት ከ2012 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ወደተግባር የሚገባ ሲሆን የክረምት ወራት የዝግጅት ምዕራፍ ሆነው እንደሚቆዩ አቶ ሀብቶም ገ/እግዚአብሔር ተናግረዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti