የአረንገዴ የአሻራ ቀንን አስመልክቶ በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ መርሀግብር ተካሄደ፡፡

Federal TVET Institute

ሀምሌ/26/ቀን 2011

በችግኝ ተከላ መርሀግብሩ ላይ አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰይፉ ታደሰ እና የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተሮች፣ አመራሮች፣ መምህራንና ሰራተኞች ተሳትፈውበታል፡፡ 

በትላንትናው እለት ከማለዳ ጀምሮ በኢንስቲትቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከ5 መቶ በላይ ሀገር በቀል ችግኞች ተተክለዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋናዳይሬክተር አቶሰይፉታደሰ እንደተናገሩት ሀምሌ 22 አረንገዋዴ አሻራ ቀንን አስመልክቶ ግራርጃርሶ ወረዳ ጫገር አካባቢበ ርካታ ቁጥር ያላቸወ ኢንስቲትዩቱ ማህበረሰብ አሻራቸውን ለማሳረፍ በነቂስ ጉዞ ማድረጋቸውን የገለጹት አቶሰይፉ በእለቱ የችግኝ እጥረት ከመኖሩ የተነሳ ችግኝ ሳይተክሉ የተመለሱ በርካታ ተሳታፊዎችን ቅር እንዳሰኘ ተናግረዋል።

ይህንን ተከትሎ በትላንትናው እለት መላው የኢንስቲትዩቱ ማህበረሰብበ እልህና በቁጭት ተነሳስተው በሴቶችና ህጻናት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ አሻራቸውን እንዳሳረፉ ተናግረዋል፡፡
በድህረ ተከላ ወቅት ችግኞችን በዘላቂነት ማጽደቅና መንከባከብ ስራ በኢንስቲትዩቱ ውስጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት እንደሚሰጠው የገለጹት አቶ ሰይፉ በቀጣይ ኢትዮዽያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እያደረገች ያለችውን ጥረት ላይ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊያደርግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡

በአገርአቀፍ ደረጃ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ዘመቻ በአንድ ጀንበር ብቻ 353 ነጥብ 6 ሚሊየን ችግኝ መተከሉ ይታወሳል።

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti