የትምህርት ፍኖተ ካርታው የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ዘርፉን ለመደገፍ በሚያግዙ ምክረሀሳቦች ዙሪያ ውይይት ተካሔደ፡፡

Federal TVET Institute

ሐምሌ25/2011

በሀገርአቀፍ ደረጃ እየተዘጋጀ ያለው የትምህርት ፍኖተካርታ የቴክኒክና ሙያ ዘርፉን ለማሳደግ ምን ማካተት ይገባዋል በሚሉ ሀሳቦች ዙሪያ የፌደራል እና የክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮዎችና ኤጀንሲዎች አመራሮች እንዲሁም የዘርፉ ተመራማሪዎች በተገኙበት በፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት ውይይት ተካሒዷል፡፡
በትምህርት ሚንስትር የትምህርና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ትግበራ ማስተባበሪያ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ በ11 ወራት የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

በሪፖርቱ እደተመላከተው ነሀሴ 14/2010ዓ/ም በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/አብይ አህመድ ለህዝብ ውይይት በይፋ ከተጀመረ በኋላ በየደረጃው ውይይቶች ተካሒዶበታል፡፡ በዚህም የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች፣ የሀይማት አባቶች እና አባገዳዎችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ውይይት አድርገውበታል፡፡

በፌደራል ደረጃ ከሰላም ሚንስትር፣ ከትራንስፖርት ሚንስትር እና ከጤና ጥበቃ ሚንስትር በስተቀር 17 ሚንስትር መስሪያቤቶች በፍኖተካርታው ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን በክልሎችም ከኦሮሚያ፣ ከትግራይና ከጋምቤላ ውጭ ካሊ ክልሎች በተገኘ መረጃ ከ2.9ሚሊየን ህዝብ በላይ ተወያቷል፡፡

እንደ አቶ ቴዎድሮስ ማብራሪያ በአጠቃላይ 357ማሻሻያ ሀሳቦች የተገኙ ሲሆን ወደ 22 በማሰባሰብ በፍኖተካርታው ረቀቂ ላይ እንዲካተቱ ለፍኖተ ካርታ ጥናት ቡድን ቀርበዋል፡፡ ከእነዚህ መካከልም 5ቱ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ላይ ያረኮሩ ናቸው፡፡

ከሪፖርት በተጨማሪም የትምህርት ፍኖተ-ካርታው ወደተግባር መግባት እንዲችል ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው እና አከራካሪ የሆኑ ሀሳቦች በተመራማሪዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ከትምህርት ፍኖተ ካርታው በቴክኒክና ሙያ መስክ አራት ምክረሀሳቦች የቀረቡ ሲሆን የመጀመሪያው ምክረ ሀሳብ አጠቃላይ ትምህርት ስርዓቱን ከሙያ ትምህርቱ ጋር ‹‹ ማካተት ›› ወይም ‹‹ ቮኬሽናላይዝድ›› ማድረግ የሚለው ነው፡፡

በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ምክረ-ሀሳብ ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 2 ያሉ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠናዎች ‹‹ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ውስጥ ቢሰጥ ›› የሚል ነው

በፍኖተ ካርታው በሦስተኛ ደረጃ የተቀመጠው ምክረ ሀሳብ አሁን እስከ ደረጃ 5 የነበረው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሥርዓት ከመጀመሪያ ድግሪ እስከ ዶክተሬት ድረስ እንዲዘልቅ የሚያስችል ነው፡፡

አራተኛውና የመጨረሻው የፍኖተ-ካርታው ጥናት የለውጥ ሀሳብ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠናውን የብቃት ማዕቀፍ የሚመለከት ነው፡፡

በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ላይ ያለው የአመለካከት ችግር በህብረተሰቡ ላይ ብቻ ሳይሆን በምሁራንም ጭምር ያለ በመሆኑ መንግስት ሰፊ የአመለካት ለውጥ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ተነስቷል፡፡

በዘርፉ ከቃላት ትርጓሜዎች ጀምሮ በሁሉም ዜጋ ዘንድ ተመሳሳይ መረዳቶች አለመኖራቸው ከፍተኛ ችግር መሆኑ በውይይቱ ተሳታፊዎች ተነስቷል፡፡

ሌላው በአጥኝዎች የተዳሰሰው የጥራት ችግር ሲሆን ችግሩን ለመፍታት ስራው ከተማሪዎች ሳይሆን ከመምህራን መጀመር አለበት፡፡ ዝቅተኛ ውጤት ያላቸውን ለመምህርነት የምንመለምል ከሆነ ጥራት ሊመጣ አይችልም የሚል መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ በተጨማሪም መምህራንን ብቻ የሚያሰለጥኑ ዩኒቨርሲቲዎች ቢቋቋሙ ለጥራቱ ወሳኝ ሊሆን እንደሚችል ተጠቆሟል፡፡

በመጨረሻም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ድኤታው ዶ/ር አብዲዋሳ አብዱላሒ የተገኙት ግብአቶች ገንቢ መሆናቸውን ጠቅሰው ምክረሀሳቦቹ ለአጥኝ ቡድኑ እንደሚቀርቡ ገልፀዋል፡፡

የትምህርት ፍኖተ ካርታ የተገኙ አስተያየቶችን አካትቶ ነሀሴ 14/2011 ዓ/ም የመጨረሻው ረቂቅ ይቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ቴዎድሮስ ተናግረዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti