በቻይና አገር የሚገኙ ስድስት የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማት ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ለመስራት የስምምነት ውል ተፈራረሙ፡፡ The Institute signed memorandum of understanding with six Chinese higher vocational Institutes.

Federal TVET Institute

July 9, 2019

ኢንስቲትዩቱ የትምህርት ጥራት ከማሳደግና ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ሙያተኞችን ከማፍራት አንጻር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣጡን ተከትሎ በርካታ የውጭ አገራት የትምህርት ተቋማት ከኢንስቲትቱ ጋር አብሮ ለመስራትና ለመደገፍ እያሳዩት ያሉት ፍላጎት እና ተነሳሽነት እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል፡፡ ከእነዚህ መካከል በቻይና የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማት ይገኙባቸዋል፡፡
በቻይና የሚገኙ ስድስት የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ውል የተፈራረሙ ሲሆን በኢንስቲትዩቱ በኩል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ተሻለ በሬቻ ተፈራርመዋል፡፡
የኢንስትቲዩቱ አካዳሚክ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብቶም ገ/እግዚአብሔር እንደገለጹት በስድስቱም የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማት እያንዳንዳቸው በጨርቃጨርቅና ፋሽን፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ ብረታብረት ስራ፣ ኤሌክትሪካል/ኤሌክትሮኒክስና ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ትምህርት ዘርፍ ባላቸው ልህቀት ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
በቀጣይም ተቋማቱ ለኢንስቲትዩቱ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን በሚያስችሉ ዘርፎች ማለትም የአሰልጣኞችና የአመራሮች እውቀትና ክህሎት ክፍተት በመለየት የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣ ነጻ የትምህርት እድል (scholarship) እንዲያገኙ ማድረግ፣ ቤተ ሙከራዎች በዘመናዊ ግብዓቶች እንዲሟሉ በማስቻል፣ ጥናትና ምርምር እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

The desire and motivation are growing with the presence of many Foreign Educational Institutions, which are growing with increasing academic excellence and competitiveness of the institute. Among them are technical and vocational education institutions in China. 
Six higher vocational Institutes from the Republic of China signed memorandum of understanding with the Institute, Teshale Berecha, Director General of the Institute sign on the side of the Institute.
Mr. Haftom G/Egziabher, Deputy Director General for Academics told that these vocational Institutes agreed to work on Garment and Apparel Fashion, Leather and Leather Products, Metallurgy, Electric/Electrics and ICT Departments, as their center of excellence.
And they also made agreement to support the Institute to give scholarship, short-term Trainings, fulfill equipments for laboratories and other, Saied Mr. Haftom.

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti