ተመራቂ ተማሪዎች ከኢንስቲትዩቱም አልፈው ለአካባቢው ማህበረሰብ ግልጋሎት የሚሰጡበት ፕሮጀክቶችን እየሰሩ መሆኑ ተገለፀ፡፡

Federal TVET Institute

July 3, 2019

የኢንስቲትዩቱ የቢውልዲንግ ኮንስትራክሽን የትምህርት ክፍል መምህራን በተመራቂ ተማሪዎች የተሰሩ የመመረቂያ ስራዎቻቸውን /project/ ገምግመዋል፡፡
በሲቪል ዲቪዥን የቢውልዲንግ ኮንስትራክሽን ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ አባዲ እንደገለጹት ተመራቂዎች በተለይም በየካ ክ/ከተማ የሚገኙ የመንግስት ተቋማት ላይ ያሉ ችግሮችን ጥናት ካደረጉ በኋላ ችግሩን ለመፍታት አልመው ፕሮጀክቶቻቸውን ሰርተዋል፡፡
በዚህም መሰረት በደጅ አዝማች ወንድራድ መሰናዶ ት/ቤት ውስጥ ለአካል ጉዳተኞችን የመሸጋገሪያ ድልድዮች፣ ለብርሀን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የግንብ አጥር፣ በላምበረት አውቶቢስ መናሀሪያ ውስጥ የንጽህና መጠበቂያ ገንዳ፣ የካ ወረዳ 9 ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ውስጥ የኮብልስቶን ንጣፍ ተነጥፏል፤ ላምበረትና አካባቢው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ለፖሊሶች አልባሳት ማጠቢያ፣ እንግዳ ማረፊያ እንዲሁም በምግብ የስራ ዘርፍ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ የብሎኬት የተገነባ ማብሰያ እና ሌሎችም ፕሮጀክቶች እንደተሰሩ ተናግረዋል፡፡
ካለፉት የትምርት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች የሰሩት የመመረቂያ ስራዎች project ብልጫ እንዳሳዩ ተገልጿል፡፡ ይህም ለህብረተሰብ ችግር መፍትሔ አፍላቂነታቸው እየጎለበተ መምጣቱን ማሳያ ነው፡፡
እነዚህ ተመራቂ ተማሪዎች የሰሩት የመመረቂያ ስራዎቻቸውን project የቁሳቁስ፣ ግብዓትና እና የጉልበት ወጪ በገንዘብ ከሁለት መቶ ሺብር በላይ እንደፈጀ ተናግረዋል::
የቢውልዲንግ ኮንስትራክሽን መምህርት ሰሎሜ ፋንታሁን በበኩላቸው ተማሪዎች የማህበረሰቡን ቁልፍ ችግር ነቅሶ በማውጣትና መፍትሔ ለማምጣት የሰሩት ስራ ጥሩ ቢሆንም ኢንስቲትዩቱ ግብአቶችን በወቅቱ ባለማቅረቡ ትልቅ እንቅፋት ፈጥሮ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
በትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማሩ ሂደት ንድፈ ሀሳብ ላይ ያተኮረ እንደነበር የገለጹት መምህርት ሰሎሜ ግብአቶች በተገቢው ባልተመዋሉበት ሁኔታ ተማሪዎቹ የተግባር ትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን በተጠነከረ መንገድ መካሄድ አለመቻሉን ተናግረዋል
ተማሪዎች አምራች ዜጋ እንዲሆኑ በሰለጠኑበት የሙያ መስክ የሚያስፈልጋቸውንና እውቀትና ክህሎት ይዘው እንዲመረቁ ማስቻል የኛ የመምህራን ብቻ ሳይሆን የኢንስቲትዩቱም ሀላፊነትና ግዴታ ነው ብለዋል
ኢንስቲትቱ በተገቢው ጊዜና ወቅት አስፈላጊውን አቅርቦትን በማሟላት በሙያው ብቁ የሆነ የተማረ ሰው ሀይል ለማፍራት የበኩሉን አንዲወጣ አሳስበዋል፡፤
ከትምርርት ክፍሉ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል አበበ ደጀኔ ማህበረሰቡን የሚጠቅም አንድ ስራ ላይ አሻራዬን ማሳረፍ ስለቻልኩ በእጅጉን ደስታ ይሰማኛል ያለ ሲሆን እሱም የነበረውን ችግር ሲገልጽ አስፈላጊ ቁሳቁስና ግብዓቶች በጊዜው አለመሟላትና ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ project በጥራትና በተገቢው መንገድ እንዳንሰራ እንቅፋት ነበር ብሏል፡፡ 
ተመራቂ ተማሪዎች በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ ውስጥም ሻወር ቤት፣ የመጸዳጃ ቤት፣ ለተማሪዎች የጠረጼዛ ቴኒስ መጫወቻ ሰርተዋል፡፡
ትምህርት ክፍሉ በመጀመሪያ ዲግሪ መርሀ ግብር ብቁ ያላቸውን 157 ተማሪዎች ሀምሌ 6/2011 ላይ ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ መሆኑን አቶ ቴዎድሮስ አባዲ አስታውቀዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti