ኢንስቲትዩቱ ከ2ሺህ በላይ ማሰልጠኛ ማሽኖችን አግኝቷል፡፡

Federal TVET Institute

(ግንቦት2/2011)

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት ባለፉት 9ወራት ከአለም ባንክ፣ KFW፣ GIZ፣ JAMK Applied Science University እና ከሌሎች ምንጮች ጋር በፈጠረው ግንኙነት ፕሮጀክቶችን በመንደፍ የተለያዩ የስልጠና ማሽኖችና ቁሳቁሶችን አስገኝቷል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የ9ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያሳየው የጀርመን ኢንቨስትመንት ባንክ (KFW) ዋጋቸው 499ሺህ 115.20 ዩሮ የሚያወጡ 2088 የስልጠኛ ቁሳቁሶችና ማሽኞች በስጦታ ለግሷል፡፡ 

ለኢንስቲትዩቱ የልብስ ስፌት፣ ጨርቃጨርቅ እና ለቆዳ ውጤቶች ቴክኖሎጂ የትምህርት ክፍሎሎች ብዛታቸው 1666 የተለያዩ የICT ዕቃዎችና ማሽነሪዎችን የለገሰ ሲሆን ዋጋቸውም 249ሺህ 217.24 ዩሮ ነው ተብሏል፡፡

ሌላው በዚሁ ረጅ ድርጅት የተገኘው የ236ሺህ 582.77 ዩሮ ድጋፍ የተለገሰው ለኢንስቲትዩቱ ለኤሌክትሪካልና ኤሌትሮኒክስ ትምህርት ክፍል ሲሆን ሦስት መቶ ሰላሳ ሦስት (333) የሆኑ የተለያዩ ዕቃዎች እና ማሽኖች ገቢ ተደርጓል፡፡

ለእንጨት ስራ ትምህርት ክፍል የጀርመን ኢንቨስትመንት ባንክ (KFW) በስጦታ የሰጣቸው ማሽኖችና መለዋወጫዎች ብዛታው 89 ሲሆን የገንዘብ መጠናቸው 13ሺህ 315.20 ዩሮ ነው ተብሏል፡፡

እነዚህ ከረጅ ድርጅቶች የተለገሱ ማሽኖች በየስልጠኛ ክፍሎች ተደራጂተው ስልጠና እየተሰጠባቸው ይገኛል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti