የድህረምረቃ ትምህርት ቤት ካውንስል የአመቱን የመጨረሻ ውይይት በማካሔድ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ፡፡

Federal TVET Institute

(ግንቦት 1/2011)

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት የድህረምረቃ ትምህርት ቤት ካውንስል አራተኛውንና በዓመቱ የመጨረሻ የሆነውን ውይይት አካሂዷል፡፡ ካውንስሉ በዋናነት በስድስት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጡም ታውቋል፡፡


የድህረምረቃ ተማሪዎች የመመረቂያ ፕሮጀክቶችን በሚመለከት የትምህርት ክፍሎች የጥራት ሁኔታቸውን እስከመጨረሻ ድረስ እንዲከታተሉ አቅጣጫ ማስቀመጥ የመጀመሪያው አጀንዳ ነበር፡፡

ሌላው የሥርዓተ-ትምህርት (Curriculum) ክለሳ ስራ ከሌሎች በአገራችን ካሉ አቻ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተዛምዶ ጥናት ተደርጎ እንዲጠና ተወያይቶበታል፡፡

በትምህርት ቤቱ እየተሰጡ ካሉ ትምህርቶች በተጨማሪ ሌሎች አዳዲስ ትምህርት ክፍሎችን ለመክፈት የገበያ ጥናት አንደሚካሔድ በውይይት መድረኩ ተነስቷል፡፡

በኢንስቲትዩቱ በክረምት እና በተከታታይ ትምህርት ክፍለጊዜ ሲሰጥ የቆየው Leadership and Management ትምህርት በመደበኛ (Regular) ትምህርት ክፍለጊዜ ለመክፈት ዝግጅቶች የተገመገሙ ሲሆን ቀጣይ ስራዎችም በአቅጣጫ መልክ ተቀምጧል፡፡

በመድረኩ ተነስቶ በስፋት ውይይት የተደረገበት ሌላው ጉዳይ የህትመት ስራዎችን የተመለከተ ነው፡፡ ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የህትመት ስራዎችን እየሰራ ሲሆን የተማሪዎች መመረቂያ ጽሑፎች፣ ፕሮጀክቶችና አርቲክሎች የጥራት ደረጃቸው ከፍ ባለ ሁኔታ እንዲታተሙ ለማድረግ ይሰራል ተብሏል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti