ኢንስቲትዩቱ ለደቡብ ሱዳን ተማሪዎች ነጻ የትምህርት እድል ሰጠ፡፡

Federal TVET Institute

ሚያዚያ 15/2011

የደቡብ ሱዳን ኢምባሲ ለዜጎቹ በኢንስቲትዩቱ ነጻ የትምህርት እድል እንዲሰጣቸው ባቀረበው ጥያቄ መሰረት መስፈርቱን ያሟሉ የአንድ መቶ ተማሪዎች ምዝገባ ተጀምሯል፡፡
የኢንስቲትዩቱ አካዳሚክ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብቶም ገ/እግዚአብሔር ኢንስቲትዩቱ ጥራት ያለው ትምህርት የሚሰጥ፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ለማድረግ ራእይያችን ላይ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ ናቸዉ ብለዋል፡፡ 
ስለዚህም ከጎረቤት ሀገራት ጋር ኢትዮጵያ ባላት ትስስር ኢንስቲትዩታችን ነጻ የትምህርት እድል መስጠቱ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡
ኢንስቲትቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም እንደመሆኑ መጠን የመምህራንን አቅም በማጎልበት፣ የመማር ማስተማር ሂደቱን ሚያቀላጥፉ ላብራቶሪዎችን በማደራጀት በርካታ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር አቅሙን በማሳደግ ላይ እንደሚገኝም ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ አካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር፣ ተባባሪ ፕሮፌሰር ቢያድግልኝ አደመ (ፒ ኤች ዲ) እንደገለጹት ከፋካሊቲ ሀላፊዎች ጋር በጋራ በመሆን ኮርሶች በመለየት የመሸጋገሪያ ኮርስ ትምህርት ለአራት ወራት እንዲሰጥ ይደረጋል ፡፡
ኮርሱ መስጠት ያስፈለገበትን ምክኒያት ሲጠቅሱ ተማሪዎቹ መሰረታዊ ቴክኖሎጂ እውቀት እንዲኖራቸው እንዲሁም ቀጣይ ዓመት ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በደረጃ 4 ተመዝነው ብቁ የሆኑ ተማሪዎች ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የእውቀትና ክህሎታቸውን ከፍ ለማድረግ እንዲያስችል ተደርጎ የሚሰጥ ስልጠና እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ የትምህርት ዘመን ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያላቸው ትምህርት ውጤት እንዲሁም የመሸጋገሪያ ኮርሶችን ወስደው ያገኙት ውጤትና ጾታን መሰረት ባደገ መልኩ ከ14ቱም ትምህርት ክፍል በመረጡት የቴክኖሎጂ ትምህርት ተመድበው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በተያያዘም ኢንስቲትዩቱ የምስራቅ አፍረካ የልእቀት ማእከል ለመሆን የሚያደርገው ጥረት ሲሳካ ከሌሎች አፍሪካ ሀገራት ተማሪዎች የትምህርት እድል እንዲያኙ በስፋት እንሰራለን ብለዋል፡፡

 


Don't forget to visit our Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti