ኢንስቲትዩቱ ከሱማሌ ክልል ለመጡ የፖሊቴክኒክ መምህራን ስልጠና ሰጠ፡

Federal TVET Institute

ሚያዚያ 15/2011

የኢንስቲትዩቱ ቴክኖሎጂ መቅዳት፣ማላመድና ማሻገር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አያሌው ሳህሌ ከሱማሌ ክልል ለመጡ የፖሊ ቴክኒክ መምህራን ላይ ያላቸውን እውቀትና የክህሎት ክፍተት ለመድፈን ባሉን ማቴሪያሎችና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞቻችን ማሰልጠን ችለናል ብለዋል፡፡
ማኒፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ፣ ውድ ቴክኖሎጂ፣ ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣ ኤሌክትሪክ ኤንድ ኤሌክትሮኒክስ፣ዋተር ቴክኖሎጂ፣ ጋርመንት ኤንድ ቴክስታይል ቴክኖሎጂ፣ የትምህርት አይነቶች ላይ ለሰባ ስድስት ሰልጣኞች ለሀያ ተከታታይቀናትስልጠናተሰጥቷልብለዋል።
የጂግጂጋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የማኒፉክቸሪንግ መምህርት የሆነችው ሰልጣኝ ሳምራዊት አበራ ስልጠናውን አስመልክቶ በሰጠችው አስተያየት ስልጠናው ብቃት ባላቸው የሀገር ውስጥና የሀገር ውጪ መምህራንና አድቫንስድ ዌልዲንግ ማሽን በስተቀር ሌሎች ማቴርያሎች የታገዘ ስልጠና ማግኘቷ እንዳስደሰታት ተናግራለች፡፡
በመቀጠል የደገሀቡር ቴክኒክናሙያ ኮሌጅ ቢዩልዲግ ኤሌክትሪካል ኢንስታሌሽን መምህር በርከሌ ሼክ ኡመር እንደገለጸው ኤሌክትሪካልና ኤሌክትሮኒክ እና አይሲቲ ትምህርት ክፍል ውስጥ ላለፉት 20 ቀናት በነበረው ቆይታ ማቴርያሎች በተሟሉበት በርካታ አዳዲስ ነገሮችን የተማረበትና ክህሎቴን ያዳበርኩበት ሰልጠና ነው በማለት ተናግሯል፡፡
በመጨረሻም የስልጠናው አስተባባሪ አቶ ሲማሩ ኩመል እንደገለጹት አድቫንስድ ዌል ዲንግ ማሽንና ሌሎችም ማቴርያሎች ከዲፓርትመንት ሀላፊዎች ጋር በመሆን እንዲገዙልን ግዢና ንብረት ክፍል ያቀረብን ሲሆን ወቅቱን ጠብቆ ባለመገዛቱ የተፈጠረ ችግር እንደነበር ገልጸዋል፡፡

 


Don't forget to visit our other Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti