ኢንስቲትዩቱ ከአነስተኛና መካከለኛ ማኒፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ኤጀንሲ ጋር በጋራ በመሆን ከክልል ለመጡ የፖሊቴክኒክ መምህራን ስልጠናሰጠ፡

Federal TVET Institute

መጋቢት 26/2011

የኢንስቲትዩቱ የማኒፋክቸሪንግ የትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ገዛኢ አብርሀ ‹‹ከክልል ለመጡ የፖሊቴክኒክ መምህራን የሲኤን ሲ (CNC) ሌዝ ማሽን(Lathe machine) ላይ ያላቸውን እውቀትና የክህሎት ክፍተት ለመድፈን ባሉን ማቴሪያሎችና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞቻችን አማካኝነት ያለምንም ክፍያ ማሰልጠን ችለናል›› ብለዋል፡፡

ሰልጠናው ለ15 ቀናት የፈጀ ሲሆን ይህም የትምህርት ክፍሉ የማህበረሰብ አገልግሎትን መስጠት ላይ ሰፊ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሆነና ስልጠናው ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ከአነስተኛና መካከለኛ ማኒፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ኤጀንሲ የስልጠናው አስተባባሪ አቶ ስዩም ተሾመ እንደገለጹት ኤጀንሲው ክልሎች ላይ የሚገኙ ፖሊ ቴክኒክ መምህራን የሲኤን ሲ ና ሌዝ ማሽን ላይ ያለቸውን የእውቀትና የክህሎትን ክፍተት በዳሰሳ በማጥናት ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ በመሆን ስልጠናው እንዲሰጥ አድርገናል፡፡

ኤጀንሲው ይህንን አይነቱን ስልጠና ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲካሄድ ያደረገ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ ላደረጉላቸው ድጋፍና ትብብር አድንቀው በቀጣይ በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ መምህር የሆነው ሰልጣኝ ትልቅሰው ያየህ ስልጠናውን አስመልክቶ በሰጠው አስተያየት ስልጠናው የሲኤን ሲ ሌዝ ማሽን ላይ በጥሩ ሁኔታ የሰለጠንን ሲሆን አሰልጣኞቹ የሚሊግ ማሽንን ጨምረው አሰልጥነውናል በዚህም አሰልጣኞቹን ላመሰግናቸው እወዳለሁ ብለዋል፡፡

በቀጣይ አዘጋጆቹ በሚሊግ ማሽን ዚሪያ ሰፋ ያለ ስልጠና የምናገኝበት መንገድ ቢያመቻቹልን ጥሩ ነው ሲልም ተናግረዋል፡፡

 


Don't forget to visit our other Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti