አካቶ ማስተማር በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ያለበትን ሁኔታ የገመገመ መድረክ ተካሔደ፡፡

Federal TVET Institute

መጋቢት 16 2011 ዓ.ም

አካል ጉዳተኞች በሁሉም የልማት ዘርፎች ገብተዉ መስራት እንዲችሉ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ደግሞ የስልጠና ሁኔታዎች ተመቻችተዉ ወደ ስራ የተገባዉ በቅርቡ ነዉ፡፡


አካቶ ማስተማር በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ያለበትን ሁኔታ ከክልሎች የተዉጣጡ ባለሙያዎችና አመራሮች በፈደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት አስተባባሪነት ሰሞኑን ገምግመዋል፡፡

አቶ ለማ ደለለኝ የኦሮሚያ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮን ወክለዉ በግምገማ መድረኩ ላይ ተገኝተዋል፡፡ አካቶ ማስተማር በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ መጀመሩ ጥንካሬ ቢሆንም ህብረተሰቡ ይህን ተረድቶ ተጠቃሚ እንዲሆን በኩል እጥቶች እንዳሉ አንስተዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ አቶ ኦላና ሙቴ የሰልጣኝ ልማት አስተባባሪ ሲሆኑ አካቶ ማስተማር በክልሎች እምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የታዬ መሆኑን ጠቁመዉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት አካል ጉዳተኛ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ሰልጥኖ ይወጣል የሚል ግንዘቤ እጥረት መኖሩን ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ሰአት አዲስ አበባ ብቻ ዉስጥ አንድ መቶ ስድሰ ሁለት አካል ጉዳተኞች በረጅም ጊዜ ስልጠና ላይ ያሉ ሲሆን ዘጠን መቶዎች ደግሞ በዘርፉ አጫጨር ስልጠና መዉሰዳቸዉ ተነስቱዋል፡፡

አካቶ ማስተማር በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ተጠክሮ እንዲሄድ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት ለአመራሮች፣ ለአስልጣኞችና ለለሎች ባለድርሻ አካላት የሚያደርገዉን እገዛ እንደሚያሰፋ ለማወቅ ተችሉዋል፡፡

 


Don't forget to visit our other Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti