ሚንስትር ድኤታው ከኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞችና ሰራተኞች ጋር ተወያዩ፡፡

Federal TVET Institute

March 15, 2019

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር ድኤታ ዶ/ር አብዲዋሳ አብዱላሂ በፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት ተገኝተው በኢንስቲትዩቱ ቀጣይ እጣ ፈንታ ዙሪያ ከኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞችና ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሔዱ፡፡ 


ኢንስቲትዩቱ ያሉት ጠንካራና ደካማ ጎኖች ምንድን ናቸው፣ ኢንስቲትዩቱን በአገርአቀፍ ደረጃ ብቁ ተቋምና የቴክኒክና ሙያ ዩኒቨርሲቲ ለማድረግ ምን ዝግጅት መደረግ አለበት፣ የአሰልጣኞችና የሰራተኞች ዝግጅት ምን መምሰል አለበት፣ የሚሉትና የመሳሰሉት ዋና የውይይቱ ማጠንጠኛ ነበሩ፡፡

ዶ/ር አብዲዋሳ እንደሚሉት ባለፉት አምስት ወራት ኢንስቲትዩቱ ያለበት ሁኔታ የማጥናት ስራ በሚንስትር መስሪያ ቤቱ ተሰርቷል፡፡ ‹‹የተሰራውን እያበረታታን የጎደሉትን በጋራ ሆነን እንሰራቸዋለን›› ብለዋል፡፡ 

በውይይት ፕሮግራሙ ላይ ሚንስትር ድኤታው በተጨማሪ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጌታቸው ነጋሽ ተገኝተዋል፡፡ 

አሰልጣኞችና ሰራተኞች የተለያዩ ጥያቄዎችን ለሚንስትር ድኤታው አንስተው ውይይት ያደረጉ ሲሆን በቀጣይም እየተገናኙ ለመወያየት ቀጠሮ ይዘዋል፡፡


View the Video

 


Don't forget to visit our other Facebook page for other News and Updates!
https://www.facebook.com/tveti